ሀትሪክ ስፖርትን ነገም ይጠብቋት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣዎ ነገም በተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ከተፍ ብላ ለእርስዎ ውድና የተከበሩ አንባቢዋ ገበያ ላይ ትቀርባለች።

ሀትሪክ ስፖርትን ነገም ይጠብቋት
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣዎ ነገም በተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ከተፍ ብላ ለእርስዎ ውድና የተከበሩ አንባቢዋ ገበያ ላይ ትቀርባለች።
ሀትሪክ በሀገር ውስጥ እትሟ ለንባብ ስትበቃም በፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር ቆይታው ክለብ አልባ ሆኖ ቤቱ ተቀምጦ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና የመከላከያ እና የአዳማውና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች ተስፋዬ በቀለ ጃምቦ ከሀትሪክ ስፖርት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሾቹን ሰጥቷል።
ተስፋዬ በቀለ ጃምቦ የአንደኛ ዙርን በምን መልኩ ክለብ አልባ ሆኖ ተቀመጠ? በሁለተኛው ዙር ወደ መቀለ 70 እንደርታ አምርቶ እንዴት ሊጫወት ቻለ? ኢትዮጵያ ቡና በነበረው ቆይታ ለክለቡ መጫወት መቻሌ ብዙ ነገሮችን አትርፌበታለው ስለ ማለቱ እንደዙሁም ደግሞ ስለ አዲሱ ቡድኑ መቀለ እና ስለ ኮረና ቫይረስ ይናገራል።
ሀትሪክ ስፖርት ሌላ የምታቀርብሎት መረጃ THE BIG INTERVIEW በሚለው ተወዳጅ አምድ የጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተርና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሀቅ በላይ ከባህር ዳር ከተማው ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ጥልቅ እና ሰፋ ያለ ቆይታን በማድረግ የሚወዱትን ቃለ ምልልስ አድርጋለች።
ሀትሪክ ከአሰልጣኝ ፋሲል ጋር በምን በምን ጉዳዮች ላይ አውርታ ይሆን? በአሁን ሰዓት ለዓለም ስጋት ስለ ሆነው ኮሮና ቫይረስ ስለ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስለሚያሰለጥነው ባህር ዳር ከተማ ስለ ደጋፊዎቹና ስለራሱ የአሰልጣኝነት ህይወት ጉዞና ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርቦለት ለሁሉም ጥልቅ ምላሽን ሰጥቷል።

ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም በአሁን ሰዓት ከፍተኛ ዋጋ ከተተመነላቸው ተጨዋቾች መካከል በ8ኛ ደረጃ ላይ ስለተቀመጠው ሊዮኔል ሜሲ ስለ አርሰናሉ ሒክቶር ቤለሪንና ፈገግታ ከፊቱ ስለማይጠፋው የሊቨርፑሉ ወርቃማ ተጨዋች ሮቤርቶ ፊርሚኖ እና ሌላም የሚወዷቸው መረጃዎች አላት።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪም ከፍተኛ መሻሻልን ባሳየውና በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋም hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
ሀትሪክ አታምልጦት
የሀትሪክ የፊት ለፊት ገጿም ይህንን ይመስላል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team