ሀትሪክ ስፖርትን ረቡዕ በገበያ ላይ ሀትሪክን በነገው እትም ጠብቋት

ሀትሪክ ስፖርትን ረቡዕ በገበያ ላይ
ሀትሪክን በነገው እትም ጠብቋት
ሀትሪክ በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት ዘ ቢግ ኢንተርቪው አምድ የባህር ዳር ከተማውን የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ፍፁም አለሙን የጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ በኳስ ህይወቱ እንደዚሁም ደግሞ ከክለቡ ጋር በተያያዘ እና ስለ ወቅታዊው ኮቪድ 19 እና ከእግር ኳስ ስለመራቅ ጠይቆት ምላሽን ሰጥቷል። ፍፁም ምን ብሎ ይሆን?
” ረጅም ጊዜ ያለ ኳስ ማሳለፍ በጣም ያማል፤ ያስጨንቃልም” የሚለው ሲጠቀስ ሌሎችም ብዙ ምላሾች አሉት።
ከሀትሪክ ሌላ ዘገባ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡናው ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃንም ስለ ራሱ ስለ ኢትዮጵያ ቡናና በጣም ስለሚያደንቀው ተጨዋችም ይናገራል።
ፍቅረየሱስ ለሀትሪክ ከተናገረው ሀሳብ ውስጥ ለቡና መጫወትና በካሳዬ መሰልጠንም የተለየ ደስታ ይሰጣል ይላል።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምንን ታስነብቦት ይሆን?
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ የሊቨርፑሉ ቨርጅል ቫንዳይክ ክለባቸው ለታሪካዊው ድል ስለመቃረቡ የማንቸስተሩ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ የፖግባ ሀሳብ ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ነው ስለማለቱ እና ሁለቱም ደስተኞች ስለመሆናቸው እና ሌሎች በርካታ መረጃዎችን ታቀርብሎታለች።
ሀትሪክ አታምልጦት።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team