ሀትሪክ ሰሞነኛ | 13ኛ ሳምንት የክለቦች ውጤት ትንተና

ወደ ድል ለመመለስ የተቸገረው እና አሳዛኝ ተሸናፊው ሀድያ ሆሳዕና

በአዲሱ አሰልጣኝ ፀጋየ ኪዳነማርያም እየተመራ ወላይታ ድቻን አሰጨንቆ 1-0 የተሸነፉት ነብሮቹ። አፍወርቅ ሀይሉ በሚጥላቸው በርከት ያሉ ያለቀላቸው ኳሶች አጋጣሚዎች መፍጠር ቢችሉም በተለይም የሁለተም ፒስማርኮች የነበረው ደካማ ወደ ግብ የመለወጥ አቅም ዋጋ ያስከፈላቸው ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር በሊጉ ለመቆየት የግብ አስቆጣሪነት ችግር መቅረፍ እንዳለባቸው አስተምሮ ያለፈ ጨዋታ ሆኗል። ነብሮቹ አሁንም በ9 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

 

 

አስደናቂው የቅዱስ ጊዮርጊ አሸናፊነት ጉዞ

ፈረሰኞቹ በዚህ ሳምንት ወልዋሎን በሰፊ የግብ ልዩነት 4-1 በማሸነፍ ተከታታይ አራተኛ ድላቸውን አስመዝግበዋል። ከፍተኛ ጫና ውስጥ የነበሩት ሰርዳን በቡድናቸው አመርቂ ውጤት እፎይታን አግንተዋል። በተለይ አቤል ያለው እና ጌታነህ ከበደ የሚያደርጉት አስፈሪ ጥምረት ለቡድኑ አስደናቂ ጉዞ ከፍተኛ ድርሻውን የሚወስዱ ናቸው። ቡድኑ በ14ኛ ሳምንት ወደ ጎንደር አቅንቶ ከተከታዩ ከፋሲል ከተማ ጋር ተጫውቶ ድል የሚቀናው ከሆነ የመጀመሪያው ዙር በአንደኝነት የማጠናቀቅ ሰፊ እድል ይኖረዋል።

 

 

መላ ያጣው የባህርዳር እና ሲዳማ ቡና ተከላካይ መስመር

ግብ የማስቆጠር ችግር የማይታይባቸው ሁለቱም ቡድኖች። በቀላሉ የሚጋለጠው ተከላካይ መስመራቸው በየጨዋታዎች በርከት ያሉ ግቦችን ለማስተናገድ እየተገደዱ ይገኛሉ። በዚህ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ተጋጣሚዎቻቸውን በተመሳሳይ 3-2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ቢችሉም። ሶስት ነጥብ ለማግኘት ግን እጅጉኑ ተፈትነዋል። በተለይም ግብ አግብተው ግብ በቀላሉ የሚያስተናግዱት ሁለቱም ቡድኖች ያላቸውን ደከማ የመከላከል አቅም ከሜዳ ውጭ ነጥብ ይዘው እንዳይመለሱ እያደረጋቸው ይገኛል።

 

 

በተከታታይ 8 ጨዋታዎች ድል ያልቀናው ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ

ድሬዳዋን በጁኒያንስ ኒያንጂቡ ግቦች 2-0 ካሸነፈ በኋላ ሙሉ ሶስት ነጥብ የተሳናቸው ቢጫ ለባሾቹ። ቡድኑ ከዮሀንስ ሳህሌ ጋር ያለየለት ውዝግብ ለውጤቱ ተፅእኖ ቢኖረውም። የፊት መስመራቸው ኳስ እና መረብን ለማገናኘት ሰንበትበት ከማለቱ ባሻገር የመከላከል መስመራቸው በቀላሉ እያፈሰሰ በሶስት ጨዋታዎች 10 ግቦች አስተናግዶ ጉዟቸውን አስከፊ እያደረገባቸው ይገኛል።

 

በዚህ አመት ከሜዳው ውጭ ሶስት ነጥብ ያሳካው ፋሲል ከተማ

በዚህ አመት ከሜዳ ውጭ ነጥብ ይዞ የመመለስ ችግር አለበት ተብሎ በደካማ ጎን ሲነሳበት የነበረው ፋሲል ከተማ። ወደ ትግራይ አቅንቶ ተፎካካሪው መቐለ 70 እንደርታን በሙጂብ ቃሲም ሁለት ግቦች 2-0 በማሸነፍ። የዚህ አመት የመደመሪያ የሜዳ ውጭ ድሉን አስመዝግቧል።

 

 

ግብ ለማስቆጠር እየተቸገረ ያለው ሀዋሳ ከተማ

ሀይቆች ከሜዳ ውጭ ነጥብ ይዘው ለመውጣት ከመቸገራቸው በተጨማሪ በተለይ በመስፍን ታፈሰ ጥገኛ የሆነው የፊት መስመራቸው ተጫዋቹ በማይኖርባቸው ጨዋታዎች ግብ ለማስቆጠር እጅጉኑ እየተቸገረ መሆኑ እያሳየ ይሆናል። በዚህ ሳምንት እንኳን ጅማ አባ ጅፋርን ቢያሸንፉም በቀይ ካርድ አንድ ተጫዋች አጥተው በጎደሎ ለ60 ያክል ደቂቃዎች ለመጫወት የተገደዱት ጅማዎች ባለሜዳዎችን ፈትነው ነው ሽንፈት ያስተናገዱት።

 

ያልተጠበቀው አስከፊው የኢትዮጵያ ቡና ጉዞ

ኢትዮጵያ ቡና ትላንት የ13ኛ ሳምት ማሳረጊያ ጨዋታ ላይ ከአዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ ነጥብ ተጋርቷል። ቡድኑ ሙሉ ሶስት ነጥብ ለማግኘት እጅጉኑ እየተቸገረ ይገኛል። በተለይም ደግሞ በሁለም ጨዋታዎች ተመሳሳይ አቀራረብ ይዞ በመቅረብ በክለቦች ተገማች እየሆነ በመምጣቱ ተጋጣሚዎችን ለማሸነፍ ችግር ውስጥ እየከተተው ይገኛል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor