ሀትሪክ ለየት ብላ መጥታለች ነገ (ረቡዕ) ማለዳ ይጠብቋት

ሀትሪክ ለየት ብላ መጥታለች
ነገ (ረቡዕ) ማለዳ ይጠብቋት
በሀገር ውስጥ
ሀትሪክ ፊቷን ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በማዞር መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ ጎራ በማለት የክለቡ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋ አሌክስ ተሰማን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ The Beg Interivew እንግዳ አደርጋ ከእናንተ ፊት ልታቀርበው ተዘጋጅታለች፡፡
ሀትሪክ ከአሌክስ ጋር በነበራት ቆይታ በክለቡ ዙሪያ የሀገር ውክልና ስለማጣታቸው ከእግር ኳሱ ወጣ በማለት ስለ ኮሮና ቫይረስና ስለ አባይ ግድብ ተናግራ አናግራዋለች ሌላው የፋሲል ከነማው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች በዛብህ መላዮንም ክለባቸው የፕሪሚየር ሊጉን ውድድር እየመራ ሊጉ በመሰረዙ እና በመጪው አመት በአፍሪካ የውድድር መድረክ የትኛውም የኢትዮጵያ ቡድን እንዳይሳተፍ ስለመወሰኑ ዙሪያና በሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎች ተጨዋቹን አናግራዋለች፡፡ የነገ ቀጠሮዎ ከሀትሪክ ጋር ይሁን ምን ይሄ ብቻ ሀትሪክ በነገው ዕትሟ የሀገር ባለውለተኛ የሆነው ተስፋዬ ኦርጌቾን ስም ከፍ አድርጋ ታነሳለች ተስፋዬ ማነው? ምን ሠርቶ አልፏል የሚለውም በወፍ በረር ልታስቃኘን ተዘጋጅታለች፡፡
ኧረ የቀረ አለ?
የተስፋዬ ኦርጌቾ የመጀመሪያዋ ልጅ በህይወት እያለሁ ተስፋዬ ልጅ የለውም በሚል በአንዳንድ ሚዲያዎች መዘገቡ ሀዘኔን የከፋ አድርጎታል፡፡ በማለትም በተለይ ለሀትሪክ ተናግራለች፡፡ በባህር ማዶ ዜናም እንደተለመደው አዳዲስና ያልተሰሙ የአርሴናሉ በርናንድ ሌኖ፣ የማን.ዩናይትዱ ሊንዶሉፍ፣ የሊቨርፑሉ ዋይናልደምና ሌሎች አዝናኝና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ዘገባዎች ተካተዋል የነገ የሀትሪክ እትሟ እንዳያመልጥዎ!!!
-ሀትሪክን ደረጃውን በጠበቀ ባለ ቀለም ጋዜጣና መፅሔት
– ከ112 ሺ በላይ ተከታዮች ባሏት የፌስ ቡክ ገፃችን
– ሀትሪክን ከ11 ሺ በላይ ተከታዮች ባሏት የቴሌግራም ቻናላችን
– ሀትሪክን ብዙ ተከታዮች ባሉት እና 24 ሰዓት ሙሉ መረጃን የሚሰጠው ድረ-ገፃችን hatricksport.net ን ይግብኙን፤
ስፖርትን እንመግባለን።
!! We Feed Sport!!

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team