ሀትሪክን ያንብቧት፤ አታምልጦት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ለንባብ ትበቃለች።

ሀትሪክን ያንብቧት፤ አታምልጦት
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ለንባብ ትበቃለች።
ሀትሪክ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
በሀገር ውስጥ:- ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈችበት ዘ ቢግ ኢንተርቪው ዓምዷ የፋሲል ከነማው አጥቂ ሙጂብ ቃሲም ከራሱ ጋር በተያያዙ እና ሌሎች ጥያቄዎች ቀርቦለት ምላሹን ሰጥቷል። በተለይ ለብሄራዊ ቡድን ባለመመረጡ ዙሪያም ያለው አለ።
“ውሳኔውና ዓላማው ባይገባኝም ከዋሊያ ውጪ መደረጌን የግድ ተቀብዬዋለሁ” ብሏል።
ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ ከኮትዲቭዋር ጋር በተደረገው ጨዋታ ለብሄራዊ ቡድናችን ጥሩ ለመንቀሳቀስ የቻለውም የሀድያ ሆሳህናው ይሁን እንዳሻውም ወቅቱን አስመልክቶና ስላለፈ አንድአንድ የኳስ ትውስታዎቹም ይናገራል።
ሀትሪክ ሌላ በርካታ የሀገር ውስጥ መረጃም አላት የቀድሞ የሐዋሳ ተጨዋቾች ማህበር ለመመስረት እያደረጉት ስላለው እንቅስቃሴና የአሌክስ ባርና ሬስቶራንት ለባለውለተኛ ስፖርተኞች እያደረገ ስላለው ድጋፍ እና ትናንት በሞት ስለተለየን ድንቁ ተጨዋች ፍቃደ ሙለታም ነፍሱን ይማረውና መረጃዎችን ትሰጦታለች።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባም ስለ ወቅቱ አነጋጋሪ እና የሜሲ አልጋ ወራሽም ሊሆን ይችላል ስለተባለው ዴጃን ሳንቾ ቴሪ ኦነሪ ስለ ኦባሚያንግ ዴብሮይኒ እና ስለ ሊቨርፑል የሊግ ክብር ይናገራል። ሀትሪክ ሌላም መረጃ አላት። አታምልጦት አንብቧት።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team