ሀትሪክን ረቡዕ ማለዳ ጠብቋት የመጀመሪያዋ ባለቀለሟ እና ተወዳጅዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ከማተሚያ ቤት ጋር በተያያዘ ችግር የቀን ለውጥ በማድረግ ረቡዕ ማለዳ በገበያ ላይ ትውላለች።

ሀትሪክን ረቡዕ ማለዳ ጠብቋት
የመጀመሪያዋ ባለቀለሟ እና ተወዳጅዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ከማተሚያ ቤት ጋር በተያያዘ ችግር የቀን ለውጥ በማድረግ ረቡዕ ማለዳ በገበያ ላይ ትውላለች።
ሀትሪክ በእዚህ ሳምንት እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ በመውጣት ታስነብቦት ይሆን?
የመጀመሪያው በአፍሪካ ክለቦች ተሳትፎ ዙሪያ የሀገር ውክልናን አስመልክቶ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሊግ ውድድሩ በመሰረዙ እና በመጪው ዓመትም ሀገራችን በማንም ቡድን የማትወከል በመሆኑ ከፋሲል ከነማ፣ ከመቀለ 70 እንደርታ እና ከሀድያ ሆሳህና እንደዚሁም ደግሞ ከሊግ ካምፓኒው የሚመለከታቸውን አካላቶች አነጋግረናል። ምላሻቸውንም ሰጥተዋል።
ሀትሪክን ረቡዕ ጠብቋት።
ሌላው የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለው በክለቡና በራሱ የኳስ ህይወት ዙሪያ ይናገራል።
አቤል ለሀትሪክ ከሰጠው ምላሽ ውስጥም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ያለ ዋንጫ! ይሄ ጊዮርጊስን አይመጥንምም ብሏል። ሌላም ያላቸውን ሰፊ ምላሾቹ ረቡዕ ያነቡታል።
ሀትሪክ ከእዚህ ውጪም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የአዳማ ከተማ ተጨዋች የሆነውን ከነዓን ማርክነህንም አናግረነዋል። የሚላችሁ አለ።
ሀትሪክ በረቡዕ እትሟ በባህር ማዶ ዘገባዋም የማንቸስተር ዩናይትዱ ሀሪ ማጉዋየር እልሜ ከዩናይትድ ጋር በርካታ ዋንጫዎችን ማንሳት ነው ሲል የሊቨርፑሉ አንዲ ሮበርትሰንምጨ ስለ ማይረሳው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት እና ሌሎች ጉዳዮችንም እያነሳ ይናገራል።
ፓውሎ ማሪም አርሰናል ከዓለማችን ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው በሚል የሰጠው አስተያየትም በጋዜጣው ቀርቦሎታል።
ሀትሪክ ረቡዕ በገበያ ላይ ትውላለችና እንዳታመልጥዎ!!

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team