ሀትሪክን ረቡዕ ማለዳ ሀትሪክ ስፖርት ረቡዕ ማለዳ በገበያ ላይ ስትውል የተለያዩ መረጃዎችን ይዛሎት ትቀርባለች።

ሀትሪክን ረቡዕ ማለዳ
ሀትሪክ ስፖርት ረቡዕ ማለዳ በገበያ ላይ ስትውል የተለያዩ መረጃዎችን ይዛሎት ትቀርባለች።
ከሀገር ውስጥ TዘE BIGINTERVIW በሚለው አምድ በአሁን ሰዓት በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ የሚገኘው የቀድሞ የደደቢት የሐዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ቡናና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች ጀማል ጣሰው ስለኳስ ህይወቱ ስለተጫወተባቸው ክለቦች ስለ ብሄራዊ ቡድን ስለ ኮከብ ተጨዋችነት ሽልማቱ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እያዋዛ ይናገራል። ጀማል ከችሎታው ባሻገር በቀልደኝነቱም የሚታወቅ ግብ ጠባቂ ሲሆን ለሀትሪክ ምርጥ ቃለ ምልልስን ሰጥቷል።
ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባ የመድን ስፖርት ክለብ
ሁለት እግራቸውን ላጡት የቀድሞ አልቢትር ዓለም ንፅበህ ኮሮና እስኪጠፋ ድረስ እርዳታ ለማድረግ ቃል ስለመግባቱና ለእዚህ እርዳታም በሸዋረጋ ደስታ የሚመራው የቀድሞ ተጨዋቾች ማህበር ስለተጫወተው ሚና ዘገባን አቅርባሎታለች።
ከዛ ውጪም የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉም ከኮቪድ 19 በኋላ ወቅቱን እንዴት እያሳለፈ እንደሆነ ስለ አሰልጣኝነት ቀጣይ ህይወቱ እንደዚሁም ደግሞ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተንለትም ይናገራል።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዳግም መመለስ እና ነገ ማታም አርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ ስለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ
ሳሙሄል ሄቶ የቀድሞ የክለብ አጋሩን ሊዮኔል ሜሲን እስከ 70 ዓመቱ ቢጫወት እንኳን የምንዝናናበት ተጨዋች ነው ስለማለቱ የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ እግር ኳስ ያለ ተመልካች ሙሉ ለሙሉ የተለየ ስፖርት ነው ስለማለቱ ስለ ባርሴሎና እና ስለ ሪያል ማድሪድ የዋንጫ ፍጥጫ እና ከመዝናኛ ውጪም ሌሎች የሚወዱትን ዘገባዎች አቅርበንሎታል።
ሀትሪክ አታምልጦት።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team