ሀብታሙ ገዛኸኝ ስለሀትሪኩ ይናገራል

👉👉 ሀትሪክ ከሰሩ አምስት ተጫዋቾች መካከል አንዱ በመሆኔ በጣም ደስታን ፈጥሮብኛል (ሀብታሙ ገዛኸኝ)

 

በቅርብ አመታት በሊጉ ከተመለከትናቸው ድንቅ ወጣት ተጫዋቾች መሀከል አንዱ የሆነው ሀብታሙ ገዛኸኝ ሲዳማ ቡና በሜዳው ወላይታ ድቻን አስተናግዶ 5-3 ባሸነፈበት ጨዋታ ተጫዋቹ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ለሀትሪክ ስፖርት የሚከተለውን ብሏል።

 

ስለዛሬው ጨዋታ እና ስለ ሀትሪክህ ምን ትላለህ ?

የዛሬው ጨዋታ በጣም ጥሩ ነበር። ሀትሪክ ከሰሩ አምስት ተጫዋቾች አንዱ በመሆኔ በጣም ደስታን ፈጥሮብኛል። ሀትሪክ በመስራቴም ይህ ለኔ ጥንካሬን የሚፈጥር ነው። ጠንክሬም እንድሰራ ያደርገኛል እንጂ እንድኩራራ አያደርገኝም።

ሀትሪክ ሰራለው ብለክ ጠብቀህ ነበር ?

ሀትሪክ እንኳን ሰራለው ብየ አልጠበኩም ነገርግን ግቦችን እንደማስቆጥር እርግጠኛ ነበርኩኝ።

ስለወቅታዊ አቋምህ እስኪ አውራኝ ?

ወቅታዊ አቋሚ ከአምናው ዘንድሮ ቀዝቀዝ ብሏል። ምክንያቱም ክረምት ዘግይቼ ወደ ዝግጅት መግባት የፈጠረብኝ ነው። እና አሁን ጠንክሬ በመስራት ወደነበርኩበት አቋሜ መመለስ ችያለው። አሁንም ጠንክሬ በመስራት ተጨማሪ ነገሮችን ለመፍጠር ሞክራለው።

በዘንድሮው አመት ከሲዳማ ቡና ጋር ምን አስበሀል ?

በዘንድሮው አመት አምና በአንድ ነጥብ ያጣናትን ዋንጫ ዘንድሮ ጠንክረን በመስራት ለማሳካት አስቢያለው።

ከዚህቀደም

ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከተማ)
እንዳለ ደባልቄ (ኢትዮጵያ ቡና)
ኦኪኪ አፎላቢ (መቐለ 70 እንደርታ)
አቡበከር ነስር (ኢትዮጵያ ቡና) ሀትሪክ የሰሩ ተጫዋቾች ናቸው።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor