ሀላባ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ

የሀላባ ከተማው አሰልጣኝ ካሊድ መሀመድ ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል።

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ እየተሳተፈ የሚገኘው የክለቡ አሰልጣኝ ከቀናት በፊት የስራ መልቀቂያ አስገብተው የነበሩ ሲሆን በክለቡ አመራሮች ተቀባይነት አግንቶ ነው ዛሬ ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን የተሰማው። ከዋና አሰልጣኙ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ በምክትል አሰልጣኝ አቶ አላምረው መስቀሌ በጊዚያዊነት ይመራል ተብሏል። ሀላባ ከተማ በ7 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ይዞ የመውረድ ስጋት ተጋርጦበት ይገኛል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor