ግብጽ ራሷን በማግለሏ ለሞሮኮው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከሩዋንዳ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ
እንዲያደርጉ ዕድል ያገኙት ዋሊያዎቹ ፕሪሚየር ሊጉ
አይቋረጥም በሚል ውሳኔ ከጨዋታው ውጪ እንዲሆኑ መወሰኑ እየተነገረ ነው።
በቀጣይ ሳምንት የ 2010 ፕሪሚየር ሊግ
ይጀመራል ተብሎ መርሐ ግብር በመያዙና የዋሊያዎቹ
ጨዋታ እሁድ በመሆኑ በመርሐ ግብር መደራረብ
የተነሳ ሊጉ አይቋረጥም ባሉ አንድ የስራ አስፈጻሚ
ውሳኔ ቡድኑ አባላት እንዱመለሱ መደረጉ ታውቋል። ከክልል የተመረጡ የቡድኑ አባላትም እንዲመለሱ እንደተነገራቸው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። የቴክኒክ ሀላፊው አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ግን “ጊዜው በማጠሩ እንዲራዘምልን ለካፍ ጠይቀን ምላሽ እየጠበቅን ነው
እንጂ ቡድኑ አልተበተነም” ሲሉ አስተባብለዋል ታማኝ መረጃዎች ግን ቡድኑ መበተኑን እየገለጹ ነው።
አስተያየት ይስጡ