መነሻ ገጽ ወልዋሎ  ዋና አሰልጣኝ ለመቀጠር ሲያመነታ የቆየው ወልዋሎ አዲግራት በመጨረሻም  አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ቀጥሯል
ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

 ዋና አሰልጣኝ ለመቀጠር ሲያመነታ የቆየው ወልዋሎ አዲግራት በመጨረሻም  አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ቀጥሯል

አጋራ
አጋራ

ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ  አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚአብሔርን ቡድኑ ካስመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት ጋር ተያይዞ ከወር በፊት ማሰናበቱ እሚታወስ ነበር። የአሰልጣኙን መሠናበት ተከትሎ ቡድኑን ማን በኃላፊነት ይረከባል እሚለው በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።

 የክለቡ የቦርድ አመራሮች አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከ 7 እሚበልጡ አሰልጣኞች ጋር ግንኙነት ፈጥረው ለመደራደር ችለዋል። በመጨረሻም ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በውጤት ቀውስ የተሰናበቱትን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ቡድኑን እዲረከቡ በኃላፊነት ሾሟል።ቦርዱ አመሻሹን ላይ አሰልጣኙን መቀጠር ይፋ መሆኑን  ተክትሎ በአንዳንድ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ እስከ አደባባይ ድረስ የዘለቀ ተቃውሞ መስማቱን ሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገጽ ከቦታው ልታረጋግጥ ችላለች።በተጨማሪም አዲሱ  አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ለአንድ ዓመት  የውል ስምምነት እንደተፈራረሙ ክለቡ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ከዚህ ቀደም በትራንስ ኢትዮጵያ፤ ሐረር ቢራ፤ ኢትዮጵያ ቡና ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ ከተማን ማሰልጠናቸው እሚታወስ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...