ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚአብሔርን ቡድኑ ካስመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት ጋር ተያይዞ ከወር በፊት ማሰናበቱ እሚታወስ ነበር። የአሰልጣኙን መሠናበት ተከትሎ ቡድኑን ማን በኃላፊነት ይረከባል እሚለው በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
የክለቡ የቦርድ አመራሮች አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከ 7 እሚበልጡ አሰልጣኞች ጋር ግንኙነት ፈጥረው ለመደራደር ችለዋል። በመጨረሻም ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በውጤት ቀውስ የተሰናበቱትን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ቡድኑን እዲረከቡ በኃላፊነት ሾሟል።ቦርዱ አመሻሹን ላይ አሰልጣኙን መቀጠር ይፋ መሆኑን ተክትሎ በአንዳንድ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ እስከ አደባባይ ድረስ የዘለቀ ተቃውሞ መስማቱን ሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገጽ ከቦታው ልታረጋግጥ ችላለች።በተጨማሪም አዲሱ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ለአንድ ዓመት የውል ስምምነት እንደተፈራረሙ ክለቡ አስታውቋል።
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ከዚህ ቀደም በትራንስ ኢትዮጵያ፤ ሐረር ቢራ፤ ኢትዮጵያ ቡና ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ ከተማን ማሰልጠናቸው እሚታወስ ነው።
አስተያየት ይስጡ