መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የካፍ ሻምፒየንስ ሊግና የኮንፌዴሬሽን ጨዋታዎች  በዳኝነት ይመራሉ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የካፍ ሻምፒየንስ ሊግና የኮንፌዴሬሽን ጨዋታዎች  በዳኝነት ይመራሉ

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በ2018 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚካሄዱ ጨዋታዎችን በዳኝነት ይመራሉ ።
የውድድሮቹ አዘጋጅ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ ለውድድሮቹ ኢትዮጵያዊያን ዳኞችን መርጧል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ ነገ  በሻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣሪያ ዳሬሰላም ላይ የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ከ ሲሸልሱ ሴንት ሉዊ ሰን የሚያደርጉትን ጨዋታ በመሐል ዳኝነት ይመራል።

ትግል ግዛው እና ክንፈ ይልማ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም አማኑኤል ኃይለስላሴ በአራተኛ ዳኛነት የኢንተርናሽናል በላይ ታደሰ ረዳቶች ይሆናሉ።

በተመሳሳይ ከነገ በስቲያ እሁድ ኪጋሊ ላይ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሩዋንዳው ኤፒአር እና የሲሼልሱ አንስ ሪዩኒየንስ የሚስተናገዱበትን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ በመሃል ዳኝነት ይመራል።

በረዳት ዳኝነት ተመስገን ሳሙኤል እና ክንዴ ሙሴ ሲገኙ፤ ቴዎድሮስ ምትኩ በአራተኛ ዳኝነት ይኖራሉ።

ኢንተርናሽናል ዳኞች በላይ ታደሰና ለሚ ንጉሴ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፊፋ የ2018 ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን በዳኝነት እንዲመሩ ከመረጣቸው ሰባት ኢትዮጵያውያን ወንድ ኢንተርናሽናል ዳኞች መካከል ይገኙበታል።

ባሳለፍነው  ታህሳስ ወር የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በሁለቱም ጾታዎች ለ22 ዋናና ረዳት ዳኞች ከፊፋ የተላከላቸውን የኢንተርናሽናል ዳኝነት ባጅ አዲስ አበባ በተደረገ ስነ ስርዓት በይፋ መቀበላቸው ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...