መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላሃዲን ሰኢድ በጀርመን የተሳካ የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉን በኢንስታግራም ገፁ ይፋ አድርጓል
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎች

ሳላሃዲን ሰኢድ በጀርመን የተሳካ የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉን በኢንስታግራም ገፁ ይፋ አድርጓል

አጋራ
አጋራ

በታሪክ ለመጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ምድብ ድልድል በገባበት ባሳለፍነው አመት 7 ጎሎችን በማስቆጠር ትልቅ ሚና የነበረው የዋሊያዎቹና የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተሰላፊው ሳላሃዲን ሰይድ በምድብ ጨዋታ ከቱኒዚያው ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ጋር ባደረገጉት ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ የሚታወስ ነበር።

በዚሁ ጉዳት ከልምምድና ከጨዋታ የራቀው ሳላሃዲን ሰይድ በቅርቡ ወደ ልምምድ ተመልሶ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከኬሲሲኤ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው እና በደጋፊው አዲስ አበባ ስታዲየም ሲያደርግ ከ8 ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ጨዋታ ተመልሶ በተጫዎተበት ዕለት ጉዳቱ በድጋሚ አገርሽቶ ወደ ውጭ ሂዶ መታከምን የሚጠይቅ በመሆኑ ፈረሰኞቹ ወደ ዩጋንዳ ለመልሱ ጨዋታ ሲያቀኑ ሳላ ለህክምና ወደ ጀርመን መሄዱ ይታወቃል፡፡

በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምናውን በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን በኢንስታግራም ገፁ ይፋ ያደረገው ሳላሃዲን ሰይድ የህክምና ክትትሉን በቅርብ አጠናቆ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ ገልጿል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...