በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት በሀገሪቱ ከፍተኛዉ የሊግ እርከን ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የነበረዉ እና በመጨረሻው የውድድር ዕለት ከሊጉ መትረፉን ያረጋገጠዉ ወልቂጤ ከተማ ከአሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራ ጋር ከተለያየ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ መሾሙ ታውቋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም በትልቅ ደረጃ በአሰልጣኝነት በሀዋሳ ከተማን ማሰልጠን የቻለዉ እና አምና ማለትም በ2014 የውድድር አመት ደግሞ ሀድያ ሆሳዕናን ለአንድ አመት ያህል ማሰልጠን ከቻለ በኋላ በውዝግብ ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት እያለዉ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ የነበረዉ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት በመጨረሻም ከአንድ አመት በኋላ ወደ ሊጉ ተመልሶ ክትፎዎቹን ለማሰልጠን በዛሬዉ ዕለት ፌርማዉን አኑሯል።