ለአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ህክምና መሳካት የህብረተሰቡና የሚዲያው አስተዋጽኦ የሚመሰገን ነው”
የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታ የሆነውን አስራት አስራት ኃይሌን ለማዳን በተደረገው ርብርብ መላው ህብረተሰብ ላደረገው አስደሳች ምላሽ ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው አመሰገነ።
- ማሰታውቂያ -
የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው እንደተናገሩት ህብረተሰቡና ሚዲያው ላደረጉት ርብርብ አመስግነው ከ50 ሺህ እስከ 450,000 ለለገሱን ሁሉም በአቅሙ ለሰጠው ምላሽ ከማመስገን ውጪ አማራጭ የለንም ይሄ ኮሚቴ እድለኛ ነው በጎ ምላሽ ለሰጡን አብረውን የቆሙትን ሁሉ እናመሰግናለን” ብለዋል።
በቱርክ ኢስታንቡል የአሰልጣኙን የህክምና ሂደት ከሚከታተለው ሞዞኬር የመጡት ዶክተር በአካል እንዳለው እንደገለጹት የአሰልጣኝ አስራት ጭንቅላት ዕጢው መታየት የጀመረው ከ3 አመት በፊት ጆሮው የመስማት ችግር ሲገጥመው በሶስት ወር በፊት ደግሞ የሰውነት ባላንስ ማድረግ ችግር ሲገጠመው ባደረገው የኤም አር አይ ምርመራ ወደ ውጪ ወጥቶ መታከም እንዳለበት በመወሰኑ ህክምናውን ለማድረግ ቱርክ ኢስታንቡል ወደሚገኘው ሆስፒታል እንዲጓዝ መደረጉን አስታውሰዋል። አሰልጣኝ አስራት ሰኔ 27/2015 ሙሉ ኦፕራሲዮን ማድረጋቸውንና የተሟላ የማገገም ሂደት ላይ እንዳሉ የገለጹት ዶክተሩ ዕጢው ወደ ካንሰር የመቀየር እድሉ ጠባብ መሆኑን ለወደፊቱ አገግመው የሚድኑበትን ቀን ግን መግለጽ እንደማይቻል አስረድተዋል። ዶክተሩ በዚህ አጋጣሚ ትብብር ያደረጉትን ኮሚቴውንና ህብረተሰቡንም አመስግኗል።
ኮሚቴው ስራውን በአንድ ወር ሰርቶ ለመጨረስ አቅዶና ተንቀሳቅሶ የተሳካ ስራ የሰራ ሲሆን ከዚህ ቀን ጀምሮ ኮሚቴው የከፈተው አካውንት የተዘጋ መሆኑንና አሰልጣኙን መርዳት የሚፈልጉ አካላት በቀጣይ በራሱ አካውንት እንዲደግፉት ጠይቋል።
እንደኮሚቴው መግለጫ በኮሚቴውና በአሰልጣኝ አስራት አካውንት በአጠቃላይ 3.8 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጾ ዴንቨር ከተማ በሚገኙ የቀድሞ ተጨዋቾችና አንድ አካዳሚ ትልቁ 400ሺህ ብር ፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 300 ሺህ ብር የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 250 ሺህ መለገሳቸውን አስረድቷል።
ከተጨዋቾች ጋር ተያይዞ ደመወዝ ያልተከፈላቸውና የተከፈላቸው መኖራቸውን የገለጸው ኮሚቴ ከተከፈላቸው ክለቦችና ተጨዋቾች ወደ 500 ሺህ ብር መሰብሰቡን ደመወዝ ከማይከፈላቸው ከወልቂጤ ከእነ ጌታነህ ከእነ አስራት ወደ 20 ሺህ ብር ገቢ መደረጉን ገልጿል።
ማስታወሻ:- ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት አሰልጣኙ አካውንት ቁጥር…
1000000117947 አስራት ሃይሌ ገብሬ