በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት በፕሪምየር ሊጉ አርባ ሶስት ያህል ነጥቦችን በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ የቻለዉ የመዲናዉ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና የአዲሱን አመት የዝግጅት ጊዜ የሚጀምርበት ቀን ታውቋል ።
በዚህም የ47 አመቱን ሰርቢያዊዉን አሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪችን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመዉ ኢትዮጵያ ቡና የፊታችን ሐሙስ ማለትም ነሐሴ-4 ወደ አዳማ ከተማ የሚያመራ ሲሆን ፤ ከማግስቱ አርብ ነሐሴ-5 ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲም ዝግጅቱን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
በተያያዘም አስከአሁን ድረስ በዝውውር ገበያዉ ላይ እምብዛም ተሳቶፎ ያላደረገዉ ኢትዮጵያ ቡና ግብ-ጠባቂዉን አስራት ሚሻሞ ማስፈረሙ የሚታወቅ ሲሆን ፤ በቀጣይ ቀናትም የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸውን የፊት መስመር ተጫዋቾች በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ስብስቡ እንደሚቀላቅል እና በተጨማሪም ሁለት የውጭ ሀገር ተጫዋቾች በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቡድኑ እንደሚቀላቅል እና በተጨማሪም ሁለት አዲስ የውጭ ሀገር አሰልጣኞችም ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ክለቡ አስታውቋል።