የ 2015 የዉድድር ዘመን በ ያሬድ ገመቹ እየተመሩ በሊጉ ያሳለፉት እንዲሁም በቀጣዩ የ 2016 የዉድድር ዘመን ደግሞ ዮሀንስ ሳህሌን አዲስ አሰልጣኝ አድርገዉ የቀጠሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸዉን መቼ እንደሚጀምሩ ታዉቋል።
የፊት መስመርዉን አጥቂ ዳዋ ሁቴሳን ጨምሮ ለቀጣይ የዉድድር አመት ስብስባቸዉን ለማጠናከር ተጫዋቾችን እያስፈረሙ እንዲሁም የነባር ተጫዋቾቻቸዉን ኮንትራት እያደሱ የሚገኙት ሀድያዎች ነሐሴ 5 ተጫዋቾች በክለቡ መቀመጫ ከተማ ሆሳዕና በሚገኘዉ የክለቡ ፅፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት የሚያደርጉ ሲሆን ነሐሴ 6 በይፋ የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸዉን እንደሚጀምሩ ተሰምቷል።