የ2015 ዓ.ም የሴቶች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዉድድር ሻምፒዮን መሆነ የቻለዉና ኢትዮጵያን ወክሎ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ዉድድር ላይ ተሳታፊ የሆነዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን ወደ ዩጋንዳ ይዞ የሚያመራዉን ልዑኩን ይፋ አድርጓል።
በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው እየተመሩ በሀዋሳ እና በአዲስ አበባ ከተማ 25 ተጫዋቾችን ይዘዉ ዝግጅታቸዉን ሲያደርጉ የነበሩት ንግድ ባንኮች ከስብስባቸዉ ላይ 5 ተጫዋቾችን በመቀነስ 20 ተጫዋቾችን እና 10 የኮቺንግ ስታፍ እና የክለብ አመራሮችን ይዘዉ በዛሬው እለት ከቀኑ 9:00 ሰአት ወደ ዩጋንዳ በረራ እንደሚያደርጉ ታዉቋል።
በዚህም መሰረት ንግድ ባንክ ወደ ዩጋንዳ ይዟቸው የሚጓዘዉ የክለቡ አባላት ስም ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱት ናቸዉ።
- ማሰታውቂያ -
ግብ ጠባቂዎች
ንግስት መዓዛ
ታሪኳ በርገና
ተከላካዮች
ናርዶስ ጌትነት
ብዙዓየሁ ታደሠ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
መሰሉ አበራ
ብርቄ አማረ
ድርሻዬ መንዛ
እፀገነት ብዙነህ
አማካዮች
ንቦኝ የን
እመቤት አዲሱ
ሰናይት ቦጋለ
መሳይ ተመስገን
ብርቱካን ገብረክርስቶስ
አጥቂዎች
ሎዛ አበራ
መዲና ዐወል
አረጋሽ ካልሳ
ሴናፍ ዋቁማ
ትንቢት ሳሙኤል
አርየት ኦዶንግ
የአሠልጣኝ ቡድን አባላት
ዋና አሠልጣኝ ብርሀኑ ግዛው
ምክትል አሠልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ
የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ንጉሴ ወ/አማኑኤል
የቡድን መሪ ተሾመ መተኪያ
ፊዚዮቴራፒስት ስንታየሁ ተሾመ
የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ቃልኪዳን ዘገየ