የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዉድድድ ዘመን ላይ በተለያዩ ዘርፎች ኮከብ የሆኑ አሸናፊዎች ሽልማቶቻቸዉ የሚሰጣቸዉን ቀን ሊግ ካምፓኒው አሳዉቋል።
የ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን የእጣ ማዉጣት ስነስርዓት ከደቂቃዎች በፊት የተደረገ ሲሆን የሊግ ካምፓኒዉ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፉ የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቦች ሽልማት ነሀሴ 13 በሀያት ሪጀንስ ሆቴል እንደሚካሄድ ገልፀዋል።
አክለዉም ሽልማቱ “በስያሜ መብት መጓተት” ምክንያት ሳይካሄድ መቆየቱን ገልፀዉ በዕለቱ ሶስት ታላላቅ ስምምነቶችን ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።