በዛሬው እለት የቡድኑ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተስፋሁን ታዲዮስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት እና ዋንጫው አርብ እለት ወደ ወላይታ ሶዶ እንደሚሄድ እና አቀባበል እንደሚደረግ ገልፀዋል ።
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን አድርገው ሲዳማ ቡና 2-1 በሆነ ውጤት ጨዋታውን ቢያሸንፍም ተገቢ ያልሆነ ተጨዋች በማሰለፋቸው ውጤቱ በፎርፌ ለወላይታ ድቻ እንዲሰጥ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን ቡድኑም በነገው እለት ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት እንደሚቀበሉ የቦርድ ሰብሳቢው ገልፀዋል።



