በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ነሀሴ 28 ለሚኖራቸው የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ወደ አክራ የሚያቀኑት የዋልያዎቹ ስብስብ ከማለዳዉ አስራ ሁለት ሰዓት አስቀድሞ ቁርሳቸውን የተመገቡ ሲሆን በዚህ ሰዓት ኤርፖርት በመገኘት ወደ አውሮፕላን ገብተው ጉዟቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ። ከ5 ሰዓታት በረራ በኃላ ጋና አክራ እንደሚደርሱ ይጠበቃል ።
በአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ የተመረጡት የመጨረሻ 23 ተጫዋቾች ዛሬ ረፋድ ወደ ጋና ከተጓዙ በኋላም የፊታችን ቅዳሜ በ29 ወደ ሀገራቸዉ በመመለስ በቀጣዩ ሳምንት የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ከዚምባቡዌ ጋር በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።

አስተያየት ይስጡ