በካሜሩን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘዉ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የነበረዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተ ከዝግጅ ጀምሮ እስከ ስንብቱ ድረስ የነበሩ ጉዳዮችን እና አጠቃላይ ስለ ካሜሩን ቆይታቸዉ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘዉ የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከመግለጫው አስቀድሞ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ብሔራዊ ቡድኑ በካሜሩን ያስመዘገበዉ ዉጤት አስደሳች ባለመሆኑ ምክንያት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ማለት እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን ፤ በመቀጠል የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ዝግጅታቸውን እንዲሁም በዉድድሩ ላይ የነበራቸዉን ቆይታ አስመልክቶ ሰፋ ያለ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ካነሷቸዉ ነጥቦች መካከልም :-
° በቅድሚያ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገን ነበር ፤ ነገር ግን ከፌዴሬሽኑ ጋር ተነጋግረን ተጨማሪ 3 ተጫዋቾችን አካተን አጠቃላይ 28 ተጫዋቾችን ይዘን ነዉ ወደ ካሜሩን የተጎዝነዉ በበረራችን ወቅት አንድ ተጫዋች በመታመሙ ምክንያት ቀንሰን በምትኩ ሌላ ተጫዋች ወደ ስብስባችን ቀላቅለናል።”
° ከወዳጅነት ጨዋታ ጋር ተያይዞ አስቀድመን ሶስት ጨዋታዎችን ለማድረግ አቅደን የነበረ ቢሆንም ሁለቱ ማለትም ከሞሮኮ እና ዙምባቡዌ ጋር ልናደርጋቸዉ የነበሩ ጨዋታዎች ሳይሳኩ በመቅረታቸዉ ከሱዳን ጋር ብቻ ተጫዉተን ወደ ዉድድሩ ለመግባት ተገደናል።”
° ከሞላ ጎደል ቁጥሮችም እንደሚያሳዩት ጥሩ ነገር ነበረን ማለት እችላለሁ ፤ በዚያዉ ልክ ክፍተቶችም ነበሩብን በዉድድሩ ላይ እንደታየዉ የመጀመሪያዉ የኬፕ ቨርዲን ጨዋታ ዉጤት የቀየረው የቀይ ካርዱ ሁነት ነዉ ። ከካሜሩን ጋር በነበረን ጨዋታ እንዳያችሁት ጥሩ 45 ደቂቃን አሳልፈን ነበር ነገር ግን ከእረፍት መልስ ክፍተቶች ነበሩብን ተጋጣሚያችን ደግሞ ጠንካራ ቡድን ነዉ ያንን ክፍተት ተጠቅሞ አሸንፎናል። አጠቃላይ ሁለቱ አጋማሾች የተለያዩ ነበሩ። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ወቅት ድንቅ እንቅስቃሴ ነበረን አስቀድመን ከተጫወትናቸዉ ሁለት ጨዋታዎች የተሻልን እንደነበርንም ቁጥሮች ይናገራሉ።”

በየጨዋታው ይጠቀሟቸዉ ስለነበሩ ተጫዋቾች ?
° ሁሉም ጨዋታዎች ተመሳሳይ አይደሉም የየራሳቸዉ ባህሪ አላቸዉ ለእያንዳንዱ ጨዋታ የሚኖረን ዝግጅት እንደየቡድኖቹ ይለያያል። ለምሳሌ በመጨረሻዉ ጨዋታ ይሁን እንዳሻው የገባዉ የተጋጣሚያችንን የጨዋታ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል አስቀድመን ስላየን እና መሐል ክፍል ላይ ተጨመሪ ሀይል ያስፈልገን ስለነበር ነዉ ።”
ፊት መስመር ላይ ስለሚሰለፉት ተጫዋቾች ?
° ሶስቱም የፊት መስመር ተጫዋቾቻችን ወደ መሐል እየገቡ እንዲጫወቱ ፍላጎት ነበረን ፤ ለምሳሌ በካሜሩን ጨዋታ ጌታነህ ትንሽ ህመም ስለነበረዉ ተጠባባቂ ነበር አበበከር በሀሰተኛ ዘጠኝ ቁጥር ተሰልፎ ነበር በዚህም ጥሩ ነገር ነበረን።”
ለእያንዳንዱ ጨዋታ ስለሚያደርጉት ዝግጅት ?
“ከጨዋታ በፊት ሁልጊዜ በሚገባ ተዘጋጅተን ለተጫዋቾች ተገቢዉን ትምህርት እንሰጣለን ተጋጣሚን በመምን አይነት መንገድ ማቆም እንደምንችል ፣ ምን አይነት የጨዋታ መንገድ ብንከተል ዉጤት እንምንይዝ ምናምን በሚገባ ለመዘጋጀት እንሞክራለን ነገር ግን አፈፃፀም ላይ ችግር አለ ።በወረቀት የሰራነው ነገር ሜዳ ላይ አለመተግበሩ ነዉ ችግሩ።”
ስለ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች አለመካተት ?
° ሰበብ ብፈልግ ኑሮ ፖስፖርት ምናምን ብየ መመለስ እችላለሁ እንደሚታወቀው ሀገራችን ሁለት ዜግነት አትፈቅድም ነገር እኔ እንደዛ አላደረኩም ፤ የተላኩልኝን የተጫዋቾች ቪዲዮ ለመመልከት ምክሬያለሁ። በቃ አጥጋቢ ሁኖ ስላላገኘሁት ነዉ ።”
አጠቃላይ ስለ ሀገራችን ተጫዋቾች ተክለ ሰዉነት ጉዳይ ?
° የሀገራችን ተጫዋቾች መስራት ይጠበቅባቸዋል ። ይሔ በ15 ቀን ምናምን የሚለወጥ ነገር አይደለም ተጫዋቹ ስራየ ብሎ ሲሰራ ያኔ የሚሻሻል ነገር ነዉ ። ነገር ግን አሁን ባለዉ ሁኔታ የሀገራችን ተጫዋቾች የፊትነስ ስራ እንደሚያስፈልጋቸዉ የአፍሪካ ዋንጫው በሚገባ አስመልክቶናል።”

በቂ የወዳጅነት ጨዋታ አለማድረጋቸው ስላሳደረባቸዉ ተፅዕኖ ?
° በዕቅዳችን መሰረት ሶስቱንም የወዳጅነት ጨዋታዎች አድርገን ቢሆን ኖሮ ጥሩ አስተዋጽኦ ይኖረዉ ነበር ብየ አስባለሁ ፤ ነገር ግን የወዳጅነት ጨዋታዎች በማነሳቸዉ ምክንያት በነጥብ ጨዋታዎች ለመማር ተገደናል።
አጠቃላይ አቅደነዉ የነበረዉ ነገር ከምድብ ማለፍ ነበር ይሄ ባለመሳካቱ ደስተኛ አይደለሁም ፤ ነገር ግን በነበረዉ እንቅስቃሴ አንድ አንድ ቁጥሮች እንደሚገልፁት ጥሩ ነገር ነበረን።
በዚህም ሲደግፉን ለነበሩት የመንግስት አካላት ፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደርሽንን ፣ ህዝቡን የሚዲያ አካላትን አጠቃላይ ማመስገን እፈልጋለሁ። ሲሉ ሀሳባቸዉ ቋጭተዋል።”
አስተዳደራዊ ጉዳኖችን በተመለከተ ደግሞ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ካነሷቸዉ ነጥቦች መካከልም :-
° በፌዴሬሽኑ በኩል ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ሳዉዲ አረቢያ ሒዶ ዝግጅት እንዲያደርግ ነበር ያሰብነዉ ከሳዉዲ የእግርኳስ ፌደሬሽን ጋርም ተነጋግረን ነበር ነገር ግን በCOVID-19 ክልከላ ምክንያት ወደዛ ሜቅናት አልቻልንም ከዛም በዘለለ ወደ ጋቦን እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ለመሔድ እና እዚያ ለመዘጋጀት ያደረግነዉ ጥረት ባለመሳካቱ ወደ አዘጋጇ ሀገር ካሜሩን አምርተናል።”
° ያቀድናቸዉ የወዳጅነት ጨዋታዎች ባለመሳካታቸዉ ምክንያት በፌዴሬሽኑ በኩል በተደረገ ጥረት በካሜሩን ከሚገኙ ጠንካራ ክለቦች ጋር ብሔራዊ ቡድኑ እንዲጫወት አመቻችተን የነበረ ቢሆንም አሰልጣኞቹ ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ ቀርቷል።
° አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ እስከ መስከረም 30 2014 ዓ.ም ዉል አላቸዉ እኛም ዉሉን እናከብራለን ስለዚህ አሰልጣኙ በስራ ገበታቸው ላይ ይቆያሉ።”
አስተያየት ይስጡ