መነሻ ገጽ ከ23 አመት በታች ኢትዮጵያ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች
ከ23 አመት በታችዜናዎች

ኢትዮጵያ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች

አጋራ
አጋራ

የኢትዮዽያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጋጣሚን ማግለል ተከትሎ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለች።

ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተጋጣሚ የነበረችው ዩጋንዳ ከውድድሩ ራሷን ማግለሏን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በዛሬው ዕለት መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በዩጋንዳ ራሷን ማግለል ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው የማጣሪያ ዙር ከሞሮኮ አቻው ጋር የሚገናኝ ሲሆነወ የመጀመሪያው ጨዋታ ጥቅምት 30 ቀን እንዲሁም የመልሱ ጨዋታው ህዳር 8 ቀን ይካሄዳል።

42 ብሔራዊ ቡድኖች በሚሳተፉበት ማጣሪያ ሶስቱንም የማጣሪያ ዙሮች የሚያልፉ ሰባት ሀገራት ከአዘጋጇ ግብጽ ጋር በመቀላቀል በአፍሪካ ዋንጫው ላይ ይሳተፋሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...