በትላንትናው ዕለት በተጠናቀቀዉ የመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ15 ጨዋታዎች 28 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ማስፈረም ችሏል።
በዚህም የፈረሰኞቹ ቀዳሚ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ፈራሚ መሆን የቻለዉ ተጫዋች ታምራት እያሱ ከዚህ ቀደም ለአርባምንጭ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን በያዝነዉ የውድድር ዘመን ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ክለብ ለሆነዉ ነገሌ አርሲ በመጫወት ላይ ይገኝ የነበረ ሲሆን ፤ አሁን ግን ከወራት ቆይታ በኋላ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማምራቱ ታውቋል።