By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ” የኢትዮጵያ እግርኳስ ህልውና በከተማ አስተዳደር የበላይ ጠባቂዎች መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ቅር ያሰኛል” ” ያለኝን የሻምፒዮንነት ልምድ ለልደታ ክ/ከተማዎች ማሳየት እፈልጋለሁ” አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችቃለመጠይቅ

” የኢትዮጵያ እግርኳስ ህልውና በከተማ አስተዳደር የበላይ ጠባቂዎች መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ቅር ያሰኛል” ” ያለኝን የሻምፒዮንነት ልምድ ለልደታ ክ/ከተማዎች ማሳየት እፈልጋለሁ” አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

በተጨዋችነት ለአማራ ውሃ ስራ፣ ለቴክስታይል፣ ለባህርዳር ከተማ ፣ ለባህርዳር ዩኒቨርስቲና ለጥቁር አባይ ተጫውቷል ። የ1ኛ ደረጃ ኮርሶችን የወሰደ ሲሆን ሲ. ቢ እና ኤ ላይሰንስ አግኝቷል.. በስልጠናውም አለም ባህርዳር ከተማ፣ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ፣ በ2000 ሚሊኒየም በ25ቱ ክለቦች ጊዜ የተስፋዬ ኡርጌች ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ ባህርዳር ዩኒቨርስቲን በፕሪሚየር ሊጉ ማሰልጠን ችሏል… የጥረት ሴቶችም ስልጠናውን አግኝተዋል… የአማራ ውሃ ስራዎች ድርጅትን ለአራት አመታት አሰልጥኖ ሁለት አመታትበተከታታይ የምድቡ ሻምፒዮን አድርጓቸዋል….ከሰምኑ ልደታ ክፍለ ከተማን ለማሰልጠን ከጫፍ የደረሰው እንግዳችን አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ ከባልደረባችን ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል…

ሀትሪክ:- የኤ ላይሰንስ ከወሰዳችሁ ቆያችሁ አይደል..?

እንዳወቀ: በርግጥ ቆይቷል…ተጨማሪ የማሻሻያ ኮርስ መውሰድ ነበረብን… ውጪ ወጥተን ስልጠና የማግኘት እድልም አላገጠመንም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይህን ማድረግ ነበረበት.. ያው ራሳችንን እያበቃን ግን እየታገልን እንገኛለን…

 

- ማሰታውቂያ -

ሀትሪክ:- እንደ አሰልጣኝ የሀገራችን እግርኳስ ላይ ተስፋ አለ ማለት ይቻላል..?

እንዳወቀ:- የሚታይ ብርሃንማ ነገር አለ… ግን ቀጣይነት ላይ ትንሽ ክፍተት አለ ግን ታዳጊ ላይ የተሻለ መሰራት አለብን እኔ ድሮ ስጫወት ከቤቴ ወጣ ስል ሜዳ ነበር አሁን ግን አንድም ሜዳ የለም ያ ትልቅ ጉዳት ነው መንግስት ኮንዶምኒየም ሲሰራ ይሄንን የሜዳ ጉዳይ ታሳቢ አለማድረጉ ቅር ያሰኛል ይሄ ጉዳት አለው

ሀትሪክ:- ብሄራዊ ቡድናችን ከሀገር ውጪ ወጥቶ መጫወቱ እንደ አሰልጣኝ ቅር አያሰኝም..?

እንዳወቀ:- በጣም ያማል ሳስበው ይከፋኛል ስደተኛ ቡድን መሆኑ በጣም ያስከፋል…120 ሚሊዮን ህዝብ ይዘን አንድም ደረጃውን የጠበቀ ሜዳ አለመኖሩ ያስከፋል። በየ ክልሉ የተጀመሩ ሜዳዎች ቢኖሩም አንዱንም አለመጨረስ ያበሳጫል ብሄራዊ በድን በሜዳው ቢጫወትኮ የደጋፊውን ጥቅም ያገኝ ነበር ውጤቱ ለመጥፋቱ አንዱ ምክንያት ከሜዳ ውጪ መሆኑ መታሰብ አለበት… ሜዳ አለመኖሩ ለመልካም ስማችን አይሆንም

ሀትሪክ:- ባህርዳር ዩኒቨርስቲ አለመኖሩ ምን ስሜት ይፈጥራል..?

እንዳወቀ:- ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ምርጥና ታሪካዊ ክለብ ነበር አሁን ግን ፈርሷል… አንዳንዴ የሚመጡት የበላይ ጠባቂዎች እግር ኳስ ከወደዱ ክለቡም ይቆያል ካልወደዱ ይፈርሳል በነሱ እጅና ስሜት የሚወሰን መሆኑ ቅር ያሰኛል ይሄ መስተካከል አለበት ሙገር ሲሚንቶና ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ምሳሌ ናቸው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመልስ መምጣቱ ደስ ይላል እንጂ አጠቃላይ ሁኔታው መስተካከል አለበት ባይ ነኝ የኢትዮጵያ እግርኳስ ህልውና በከተማ አስተዳደር በላይ ጠባቂዎች መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ቅር ያሰኛል።

ሀትሪክ:- የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ለእግርኳስ ያላቸው ፍቅርስ ለየት አይልም..?

እንዳወቀ:- ከንቲባው ከድር ለብዙ ከንቲባዎች ሞዴል ነው የድሬዳዋ ከተማ ክለብን እየታደገ ነው ሜዳ እየሰራ ሀገርን እየጠቀመ ነው… የተሻለ የስራ አቅም ያለው ሰው ይመስለኛል ሌሎቹ ከሱ መማር አለባቸው ክለቦችም ከከንቲባው ተሞክሮ መውሰድ አለባቸው።

ሀትሪክ:- እስቲ ስለ ልደታ ከተማ እናውራ… ?

እንዳወቀ: ልደታ ከተማ በብሄራዊ ሊግ የሚወዳደር ክለብ ነው ከ20 ክለቦች 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል.. ከሰሞኑ ሲቪዬን አስገብቻለሁ እነሱን የማሰልጠን እድሉን እንደማገኝ ተስፋ አድርጋለሁ…. አውስኮድን ይዤ የምድቡ ሻምፒዮን በማድረጌ በልደታዎች እድል እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ… በ2013 እና በ2015 በተከታታይ ሻምፒዮን ሆኛለሁ… በ2014 ደግሞ በሀገራዊ ችግር የተነሳ ውድድሩ ተቋርጧል… ይህንን ከልደታ ጋር ማስቀጠል እፈልጋለሁ ልምዴም ይጠቅመኛል…

ሀትሪክ:- የመጨረሻ ጥያቄ…ለልደታ ከተማዎች የምትለው ነገር አለ..?

እንዳወቀ:-: ልደታዎች እድሉን ቢሰጡኝ ደስተኛ ነኝ ከመሪ ክለቦች ጋር ያለውን 12 ነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል ይኖረናል… የቡድኑን ጠንካራና ደካማ ጎን አይተን ለማረም ዝውውሩ ላይም ሁለትና ሶስት ተጨዋቾችን ጨምረን ወደ ዋንጫ ፉክክር ውስጥ የማስገባት አቅም አለኝ ብዬ አስባለሁ… ገና 19 ጨዋታ አለ ከምድቡ ሁለት ቡድን ስለሚያልፍ ከቻልኩ ሻምፒዮን ሆኜ ካልሆነ ቡድኑን ሁለተኛ አድርጌ ለመጨረስና ለማሳለፍ የምችለውን እንደማደርግ ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ በአጠቃላይ ያለኝን የሻምፒዮንነት ልምድ ለልደታ ከተማዎች ማሳየት እፈልጋለሁ..

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ሲያሳካ ፤ ነብሮቹ እና ሀይቆቹ አቻ ተለያይተዋል !!
Next Article ቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችአዳማ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

“አዳማ ትልቅ ቡድን ነው፤ ድሉ እና ቡድኔን የምታደግበት ጎል ማስቆጠሬም ይቀጥላል”አብዲሳ ጀማል /አዳማ ከተማ/

መሸሻ ወልዴ By መሸሻ ወልዴ 5 years ago
“ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የምንሳተፍባቸውን በርካታ ውድድሮችን ለመሰረዝ እንገደዳለን።” “ስፖንሰሮች በመሸሻቸው ፌዴሬሽኑ ለከፍተኛ ወጪ ተዳርጓል።” የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት :- አቶ ኢሳያስ ጅራ
“ውጤት እንዲመጣ ከተፈለገ ከመፈራራት ይልቅ መከባበር ትልቁን ድርሻ ይወስዳል” ፍሬው ኃይለገብርኤል
ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት ተጫዋቾችን ከተስፋ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን አሳደገ።
ሪፖርት | የኢትዮጵያና ሌሴቶ ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?