By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ሲያሳካ ፤ ነብሮቹ እና ሀይቆቹ አቻ ተለያይተዋል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሀዋሳ ከተማድሬዳዋ ከተማወልቂጤ ከተማሀዲያ ሆሳዕና

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ሲያሳካ ፤ ነብሮቹ እና ሀይቆቹ አቻ ተለያይተዋል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በአስራ አምስተኛዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ የቀን ዘጠኝ ሰዓት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና እና ሀዋሳ ከተማ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ተለያይተዋል ።

ተመጣጣኝ በሚባል የጨዋታ እንቅስቃሴ የጀመረው የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያ ገና በመባቻዉ ግብ ተቆጥሮበታል ፤ በዚህም በ9ነኛዉ ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻገረዉን ኳስ ቃልዓብ በጭንቅላቱ ለመለሰ አቀብሎት መለሰ በመቀስ ምት ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን ሀድያ ሆሳዕና መሪ ማድረግ ችሏል። ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ የአቻነት ግብ ለማግኘት በተደጋጋሚ ጫና መፍጠር የጀመሩት ሀዋሳ ከተማዎች በ25ተኛዉ ደቂቃ እዮብ አለማየሁ ከሳጥን ውጭ አክርሮ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ያሬድ በቀለ ኳሷን መልሶበታል።

በ35ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሀዋሳ ከተማ የአቻነት ጎል አግኝተዋል ፤ በዚህም ከግራ በኩል የተገኘዉን ቅጣት ምት እዮብ አለማየሁ ሲያሻማ ከዚያም ተባረክ ሄፋሞ በጭንቅላቱ ሲገጭ ኳሱን ያገኘዉ ፀጋዓብ ዮሐንስ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል። ከዚያም በኋላ በተመጣጣኝ የጨዋታ እንቅስቃሴ በቀጠለዉ የሀለቱ ክለቦች ጨዋታ ተጨማሪ ተጠቃሽ ሙከራ ሳይስተዋልበት አጋማሹ ተጠናቋል።

- ማሰታውቂያ -

ከዕረፍት መልስ ወዲያውኑ በ50ኛዉ ደቂቃ ላይ ሀድያ ሆሳዕናዎች ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ፤ በዚህም ከማዕዘን ሳሙኤል ያሻገረዉን ኳስ ሰመረ ሀፍተይ በቀጥታ ወደ ግብ መቶት የነበረ ቢሆንም ኳሱ ለጥቂት በግቡ አናት ላይ ወጥቷል። ምንም እንኳን በጨዋታ ረገድ ብልጫ ቢወሰድባቸዉም አልፎ አልፎ በፊት መስመር ተጫዋቾቹ አሊ ሱለይማን እና እዮብ አለማየሁ አማካኝነት ተደጋጋሚ የሚባሉ ሙከራዎችን ማድረግ የቻሉት ሀይቆቹ ያን ያህል በቀሩት ደቂቃዎች ላይ አደጋ መፍጠር ሳይችሉ መርሐግብሩ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።

በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል።

አመሻሽ 12 ሰዓት ሲል በጀመረው እና ተመጣጣኝ የሚባል የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ባስመለከተን ጨዋታ ወልቂጤ ከተማዎች ከኋላ መስመር በሚላኩ ኳሶች አደጋዎችን ለመፍጠር ሲጥሩ በተቃራኒው ፤ ድሬዳዋ ከተማዎች በ12ተኛዉ ደቂቃ ላይ የተገኘዉን ቅጣት ምት በመሐመድ አማካኝነት በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክሩም ኳሷ ግን የግቡን ቋሚ ለትማ ለመልሳለች።

አልፎ አልፎ በሚገኙ አጋጣሚዎች ወደ ሶስተኛዉ የሜዳ ክፍል በመድረስ አደጋ ለመፍጠር ሲጥሩ የነበሩት ድሬዳዋ ከተማዎች በ30ኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። በዚህም አጥቂዉ ቻርልስ ሙሴጌ ከሱራፌል ጌታቸዉ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ምንም እንኳን ያን ያህል ተጠቃሽ ሙከራ ማድረግ አይቻሉ እንጅ አልፎ አልፎ በአቡበከር ሳኒ እንዲሁም ጋዲሳ መብራቴ አማካኝነት ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ የነበሩት ወልቂጤ ከተማዎች የአቻነት ግብ ሳያገኙ አጋማሹ ተጠናቋል።

ከመልበሻ ክፍል መልስ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ በማስገባት የጨዋታዉን ብልጫ ለመዉሰድ ጥረት ማድረግ የቀጠሉት ሁለቱም ክለቦች እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ ሁለቱም ቡድኖች ይዘዉት የቀረቡትን የጨዋታ መንገድ ለመተግበር እና ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ የነበረ ቢሆንም ሁነቱ ሳይሳካ ጨዋታዉ በድሬዳዋ ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ባህርዳር ከተማ እና መቻል በተመሳሳይ ተጋጣሚዎቻቸዉን 1ለ0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዘዋል !!
Next Article ” የኢትዮጵያ እግርኳስ ህልውና በከተማ አስተዳደር የበላይ ጠባቂዎች መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ቅር ያሰኛል” ” ያለኝን የሻምፒዮንነት ልምድ ለልደታ ክ/ከተማዎች ማሳየት እፈልጋለሁ” አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችየወዳጅነት ጨዋታሀዲያ ሆሳዕና

የሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ጆሀንስበርግ ላይ አደረጉ….

ዮሴፍ ከፈለኝ By ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
 ወላይታ ድቻን  ለማሰልጠን ሁለት አመታትን ለመቀጠል ፊርማውን ያኖረው አሰልጣኝ መሣይ ተፈሪ ከሀትሪክ ጋዜጣ ጋር ያደረገውን ቆይታ እንሇ !!!
” ወደ አፍሪካ ዋንጫዉ የመጣነዉ ለተሳትፎ ሳይሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ለመሻገር ነዉ።” አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ
ወደ 2014 ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ የሚደረገዉ ውድድር ነገ በሀዋሳ ድልድሉ ይወጣል
አስተያየት| መቐለ 70 እንደርታ 5-1 ሀዋሳ ከተማ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?