ባህርዳሮች ሦስተኛውን አዲስ ተጫዋች አግኝተዋል።
በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመሩት ባህርዳር ከተማዎች ከዮዳሄ ዳዊት እና ሽመልስ በቀለ በመቀጠል ሦስተኛው ፈራሚ አጥቂው ኪቲካ ጂማ ሆኗል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ፍሬ የሆነው እና በገላን ከተማ ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋች የተጠናቀቀውን አመት በመቐለ 7ዐ እንደርታ ጀምሮ በነገሌ አርሲ ያጠናቀቀው አጥቂው ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ለባህርዳር ከተማ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።
አስተያየት ይስጡ