ስፖርት ዞን የሬድዮ ፕሮግራም በስድስት ዘርፎች እና በስፖርቱ ታሪክ ለሰሩ እንዲሁም አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ያዘጋጀዉ የዕውቅና ፕሮግራም ዛሬ ምሽት ሀያ ሁለት አካባቢ በሚገነዉ ቼክ ኢን ሆቴል ይካሄዳል።
ምሽት 12:00 በሚጀምረው ፕሮግራምም ለስፖርቱ አስተዋፅኦ ያበረከቱ እና ተሸላሚ ግለሰቦች እንዱሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በስፍራው እንደሚታደሙ ይጠበቃል።

በስፖርት ዞን ዓመታዊ የሽልማት ዝግጅት ላይ የመጨረሻ እጩዎች የሚከተሉት ናቸዉ።
ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ: ሚኬል ሳማኬ፣ ባህሩ ነጋሽ እና አቡበከር ኑሪ
ተስፋ የተጣለበት ተጫዋች ዘርፍ: አቡበከር ኑሪ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዊልያም ሰለሞን
ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ: ያሬድ በየህ፣ አቡበከር ናስር፣ ሽመክት ጉግሳ
ምርጥ አሰልጣኝ ዘርፍ: ሥዩም ከበደ፣ ካሣዬ አራጌ፣ ዘላለም ሽፈራዉ
ምርጥ ዋና ዳኛ ዘርፍ: ቴዎድሮስ ምትኩ፣ በላይ ታደሰ፣ ኤፍሬም ደበሌ
ተጓዥ ደጋፊ ዘርፍ: ፋሲል ከነማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና

አስተያየት ይስጡ