በክረምቱ የተጫዋቾች የዝዉዉር መስኮት በርካታ የሚባሉ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች ዛሬ ደግሞ በዝዉዉሩ መዝጊያ ዕለት ዩጋንዳዊዩን አጥቂ ደሪክ ንሲባምቢ ማስፈረማቸዉ ወኪሉ አዛሪያ ተስፋፅዮን ለሀትሪክ ስፖርት ገልጿል።
ለሀገሩ ክለብ ካምፓላ ሲቲ እና ለግብፁ ሰሙሁ ስፖርት ክለብ መጫዎት የቻለዉ የ27 አመቱ አጥቂ የሀገሩን ብሔራዊ ቡድንም ከ17 አመት በታች ጀምሮ ማገልገል የቻለ ሲሆን ለሀገሩም በተሰለፈባቸዉ አስራ ስምንት ጨዋታዎች ስድስት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። 1ሜትር ከ74 የሚረዝመዉ አጥቂዉ ከዘንድሮዉ የዉድድር አመት አንስቶ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ ስብስብ ዉስጥ የምንመለከተው ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ