በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራዉ እየተመሩ በዝውውር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ሰበታዎች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የሁለት ተጫዋቾችን ዝዉዉር ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል።
ለደቡብ ፖሊስ ፤ መከላከያ ፤ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ረዘም ያሉ አመታትን በፈረሰኞቹ ቤት ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ ግብ ጠባቂዉ ለአለም ብርሀኑ ወደ ሰበታ ከተማ ማምራቱ እርግጥ ሆኖአል።
ሌላኛው ለክለቡ ፊርማዉን ያኖረዉ ደግሞ በሲዳማ ቡና እና ደቡብ ፖሊስ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ አዲስአለም ደበበ መሆኑ ታዉቋል። ተጫዋቹ ሰበታን ለሁለት አመት በሚቆይ ዉልም መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ