በዮሴፍ ከፈለኝ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል።

ከቀናት በፊት በተካሄደው የ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን 2ለ1 በሆነ ውጤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ማሸነፉ ይታወሳል። በጨዋታው ላይ ኢትዮጵያ መድን የማሸነፊያዋን ሁለተኛ ጎል ሲያገኙ በእጅ ተነክቷል በሚል የፍፁም ቅጣት ምት የሰጡት ፌድራል ዳኛ ሚካኤል ጣዕመ ተገቢነት የሌለውን ውሳኔ ወስነዋል በሚል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ዳኛውን ከሊጉ ጨዋታዎች አሰናብቶታል።
ከሳምንት በፊት የአዲዳስ እና ፑማን ማሊያ አድርጎ ልምምድ ሰርቷል በሚል አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ወደመጣበት እንዲመለስ ለተደረገው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባህሩ ተካ ደግሞ በድጋሚ በምትኩ ጥሪ ቀርቦለታል።
የአመቱ ውድድር ሊጠናቀቅ እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዳኞች የሚታገዙበት ቴክኖሎጂ አለመኖሩ አወያይነቱ ቀጥሏል።
አስተያየት ይስጡ