በደቡብ ሱዳኑ ጃሙስ ክለብ የሚገኙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዛሬው የዋልያዎቹ ድል በኋላ ሁለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
“በቅድመ ማጣሪያ ጨዋታችን ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔን አራት ለዜሮ በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ ምድብ ድልድል በመግባታችን ደስ ብሎኛል።ይህንን ድል ላሳኩት የቡድን አባላትም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ።

በሌላ በኩል በግሌ ስለ ብሔራዊ ቡድናችን ከታች ባሉት ነጥቦች ላይ አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ።
1ኛ ከአምስት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳችን በተመልካች ፊት እንድንጫወት ከፍተኛ ስራ በመስራት ቡድናችን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለስ ሁኔታዎችን ያመቻቹትን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድርን ከልቤ እያመሰገንኩ በቀጣይ የሚኖሩ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎችንም በሜዳችንና በደጋፊያችን ፊት እንድንጫወት የሚቻለውን ሁሉ ጥረት እንዲደረግ ማስቻል ቀጣይ የቤት ስራ እንደሆነ መጠቆም እወዳለው። ብሔራዊ ቡድናችን በሜዳው ቢጫወት የሚያገኘው በርካታ advantage እንዳለ ሆኖ ይህን ዕድል አሳልፈን መስጠት ተፅኖው ከፍተኛ እንደሆነ መገንዘብ ይገባል። ቡደናችን ለሚያስመዘግበው ውጤትም አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል።
2ኛ ምንም እንኳን በዚህ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ተጋጣሚያችንን አሸንፈን ብናልፍም ብሔራዊ ቡድናችን በየትኛውም መመዘኛ በዚህ ደረጃ መገኘት አና ከመሰል ሀገራት ጋር መወዳደር መመልከት የማይገባን የማይመጥነን በመሆኑ በቀጣይ በሚደረጉ የምድብ ጨዋታዎች ላይ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ሀገራችንና ቡድናችንን በሚመጥን ደረጃ ላይ ማስቀመጥ እንደሚጠበቅብን በማመን ሁላችንም የበኩላችንን ድጋፍ በማድረግ ከብሔራዊ ቡድናችን ወደዚህ አዘቅት እንዳይመለስ ለማድረግ ከብሔራዊ ቡድኑ ጎን እንድንሆን ማሳሰብ እወዳለሁ።” በማለት አሰልጣኙ ገልፀዋል።
አስተያየት ይስጡ