መነሻ ገጽ ዜናዎች የኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በሚገኘው በማፊ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከናውኗል
ዜናዎች

የኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በሚገኘው በማፊ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከናውኗል

አጋራ
አጋራ

 

በጉባኤው ላይ ያለፈው አመት አፈፃፀምና የአዲሱ አመት ዕቅድ ይፋ ተደርገው በክልሉ እግርኳሳዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ነጥቦችን በማንሳት ከክልሉ የተወጣጡ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ምክክር ተደርጓል። የውይይቱን መድረክ ሲመሩ የነበሩ የክልሉ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ የነበሩ አቶ ፍሮምሳ ለገሰና የፌዴረሽኑ ፕሬዘደንት አቶ ሙስጠፋ ከድር በጉባኤው ላይ ከታደሙት አካላት ጋር የተለያዩ ነጥቦችን አንስተው አወያይተዋል።

በጉባኤው ላይ የክልሉ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና አዳዲስ ስራ አስፈፃሚዎችና በመሆን ለቀጣዮቹ አራት አመታት እንዲያገለግሉ በአስመራጭ ኮሚቴ የቀረቡት 7 አባላት ያላቸው ግለሰቦች የነበሩ ሲሆን። ከ21 የክልሉ ዞኖች፣ ከ19 ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከ2 የአሰልጣኞች ማህበራትና ከ2 የአርብትሮች ማህበራት ባጠቃላይ በ40 ድምፅ ሰጪዎች ምርጫው ተከናውነዋል።

ለምርጫው የቀረቡ እጩዎች

ዶር ዋቅጅራ ስማ (ቢሾፍቱ ከተማን በመወከል)
ወ/ሮ አበራሽ ታደሰ (ቢሾፍቱ ከተማን በመወከል)
አቶ ደረጄ ሙላቱ (ነቀምቴ ከተማን በመወከል)
አቶ ግርማ በቀለ (የሰሜን ሸዋ ዞንን በመወከል)
አቶ ድንቁ አበበ (ለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ከተማን በመወከል)
አቶ ከበደ ወርቁ ሰበታ ከተማን በመወከል እንድሁም
ዶር እንደገናለም አዋስ አዳማ ከተማን በመወከል ቀርበው የነበረ ሲሆን ዶር ዋቅጅራ ስማ ለቀጣዮቹ 4 አመታት የኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት በመሆን ወ/ሮ አበራሽ ታደሰ ደግሞ ፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን እንዲያገለግሉ በጉባኤው ሙሉ ድምፅ ሲመረጡ የተቀሩት እጩዎች የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በመሆን እንዲያገለገሉ ተመርጧል።

የምርጫ ስነስርዓቱ ከተከናወነ በኋላም የቃለመሀላ ስነስርዓት በማከናወን ከቀድሞው የፌዴሬሽኑ አመራር ጋር የሰነድ ርክክብ በማድረግ አጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...