መነሻ ገጽ ዜናዎች ሁለተኛውን የስፖርት ዞን አዋርድ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል !
ዜናዎች

ሁለተኛውን የስፖርት ዞን አዋርድ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል !

አጋራ
አጋራ

 

የፊታችን መስከረም 8 በስድስት ዘርፎች ለሚካሄደዉ ሁለተኛዉ የስፖርት ዞን አዋርድ በዛሬዉ ዕለት በቤዝ ኢትዮጵያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በራዲዮ ፕሮግራም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ባሳለፍነዉ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀት የቻለዉ እና ከቀናት በኋላ ደግሞ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የሚደረገው ሁለተኛዉ የስፖርት ዞን አዋርድ ስድስት ዘርፎች እንደሚኖሩት የተገለፀ ሲሆን ከወራት በፊት በየዘርፉ በርከት ያሉ ዕጩዎች ይፋ ተደርገዉ የነበረ ሲሆን ባለፉት ቀናትም በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ምርጫ ሲካሄድ ከቆየ በኋላ የአዘጋጆቹ ምርጫ ተካቶበት በዛሬው ዕለት በየዘርፉ የመጨረሻ ሶስት ሶስት ዕጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

የመጨረሻ ዕጩዎችም :-

የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ዕጩዎች

1, ቻርልስ ሉክዋጎ
2, ሚካኤል ሳማኬ
3, አልዓዛር ማርቆስ

የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ዕጩዎች

1, በዛብህ መለዮ
2, አቡበከር ናስር
3, ጋቶች ፓኖም

ተስፋ የተጣለባቸዉ ወጣት ተጫዋች ዕጩዎች

1, እንዳልካቸዉ መስፍን
2, አልዓዛር ማርቆስ
3, ብሩክ በየነ

የአመቱ ምርጥ ደጋፊዎች ዘርፍ ዕጩዎች

1, የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች
2, የባህርዳር ከተማ ደጋፊዎች
3, የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች

የአመቱ ምርጥ ዳኞች ዘርፍ ዕጩዎች

1, ሀይለየሱስ ባዘዘዉ
2, ኤፍሬም ደበሌ
3, አሸብር ሰቦቃ

በተጨማሪም በዘንድሮው አመት ከተካተቱት አዳዲስ የዕውቅና ዘርፎች መካከልም በስፖርቱ አለም አስተዋፅዖ የነበራቸዉ የህክምና ባለሙያዎች ፣ አሰልጣኞች እንዲሁም አመራሮችን የመሳሰሉ ሌጀንዶች የሚሸለሙ ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪም በዘንድሮው አመት የስፖርት ዞን አዋርድ ላይ ከተጨመሩ የሽልማት ዘርፎች መካከል በአትሌቲክስ የቡድን ስራን ለማበረታታት በሚል የዕዉቅና ፕሮግራም እንደሚኖር ተገልጿል።

በተያያዘም የሴቶች እግርኳስ ተጫዋቾችን በተመለከተም ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ የሴቶች ኮከቦችን ለመምረጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት አሰልጣኝ ብርሐኑ ግዛውን ጨምሮ ሌሎች አራት የሚደርሱ የሴቶች አሰልጣኞች ዕጩዎችን እንዲልኩ እንደተደረገ እና በሽልማት ፕሮግራሙ ላይም በሴቶች ተጫዋቾች ዘርፍ ምርጫ እንደሚኖር ተገልጿል።

በመጨረሻም በዕለቱ ለተሸላሚዎቹ የሚበረከተውን ዋንጫ በተመለከተ በአርክቴክት ናትናኤል አማካኝነት ማብራሪያ ተደርጎበት መግለጫው ተጠናቋል። በዕለቱም የስፖርት ዞን አዋርድ ሙሉ ፕሮግራም በፋና ቴሌቭዥን ከምሽት 12 ጀምሮ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚያገኝ ተገልጿል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...