By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሻሸመኔ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስወልቂጤ ከተማየጨዋታ ዘገባሻሸመኔ ከተማ

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሻሸመኔ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

– በሊጉ የ16ተኛ ሳምንት የሶስተኛ ዕለት ቀዳሚ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን አሸንፏል ።

128ተኛዉን የአድዋ ድል በዓል በመዘከር በጀመረዉ የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ምንም እንኳን በሙከራ ረገድ ደካማ የነበረ ቢሆንም በእንቅስቃሴዉ መባቻ ላይ ግን አዲሱ ፈራሚ ታምራት በ14ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከቢኒያም በላይ የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ፈጥኖ የወጣዉ የግብ ዘቡ ፋሪስ አለሙ ኳሷን አውጥቷታል። በድጋሚ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ከቀኝ መስመር በኩል ሄኖክ አዱኛ የሞከረዉን ኳስ ተጨርፎ ሲመለስ ያገኘዉ ዳግማዊ አርአያ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የግብ ዘቡ ፋሪስ አውጥቷል።

ተደጋጋሚ ሙከራዎችን በማድረግ ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ የነበሩት ጊዮርጊሶች በአጋማሹ መገባደጃ ተከላካዩ ረመዳን የሱፍ ከቢኒያም የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ ኳሷ ኢላማዋን ሳትጠብቅ ወጥታለች ። ምንም እንኳን በጨዋታ እንቅስቃሴ የተሻለ ቢሆንም በሙከራ ረገድ ግን ሶስት ኢላማቸዉን የጠበቁ ሙከራዎች ብቻ በተደረጉበት እና ግብ ባልተስተናገደበት የመጀመሪያው አጋማሽ ክትፎዎቹ ይህ ነዉ የሚባል ተጠቃሽ ሙከራ ሳያደርጉ ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል ።

- ማሰታውቂያ -

ከዕረፍት መልስ የሁለት ተጫዋቾችን ለዉጥ አድርገዉ የገቡት ፈረሰኞቹ ዉጥናቸዉ ሰምሮ በ62ተኛዉ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ በገባዉ አማኑኤል አረቦ አማካኝነት ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል ቢኒያም ያሻማዉን ኳስ አማኑኤል አረቦ በግንባሩ ግጭቶ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ አድርጓል።

በሙከራ ረገድ ያን ያህል ባልነበሩት ክትፎዎቹ በኩል በ64ተኛዉ ደቂቃ ላይ ጋዲሳ መብራቴ ያሻማዉን ኳስ ሙሉዓለም መስፍን ወደ ግብ ቢሞክርም ባህሩ ነጋሽ ይዞበታል ። በጥሩ ፉክክር በቀጠለዉ መርሐግብር በመገባደጃዉ ወቅት በበረከት ወልዴ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ማድረግ የቻሉት ጊዮርጊሶች በጭማሪ ደቂቃ ላይ ሁለተኛዋን የማሸነፊያ ጎላቸዉን ተቀይሮ በገባዉ አልዓዛር አማካኞነት አስቆጥረዉ ጨዋታውን 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል ።

– በምሽቱ የአንድ ሰዓት መርሐግብር በወራጅ ቀጠናዉ ላይ የሚገኘዉ ሻሸመኔ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ወላይታ ዲቻን 2ለ1 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል ።

ድንቅ ፉክክር ባስመለከተን እና እንደ መጀመሪያዉ ጨዋታ ሁሉ በአደዋ ድል መዘከር በጀመረዉ የምሽቱ ጨዋታ ዲቻዎች ገና በመባቻዉ በዘላለም አባተ አማካኝነት ግብ ለማስቆጠር ተቃርበዉ ግቀሰ ጠባቂዉ አቤል ማሞ አውጥቶባቸዋል። ጫናቸዉን አጠንክረዉ የቀጠሉት ዲቻዎች በድጋሚ ከደቂቃዎች በኋላ ብስራት በቀለ ከዘላለም በተቀበለው ኳስ ድንቅ ሙከራ ቢያደርግም ኳሷ በግቡ አናት ለጥቂት ወጥታለች።

ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ የቀጠሉት ድሬዎች በ16ተኛዉ ደቂቃ ላይ ቢኒያም ፍቅሬ ከርቀት ድንቅ ሙከራ አድርጎ ግብ ዘቡ አቤል ሲያወጣበት በድጋሚ በ33ተኛዉ ደቂቃ ላይ አብነት ደምሴ በግንባር ሞክሮ ኳሷ ለጥቂት ወጥታለች ። በመጀመሪያዉ አጋማሽ መገባደጃ ወቅት በ45ተኛዉ ደቂቃ ላይም ኬኔዲ ከበደ ከቀኝ መስመር በኩል ያሻገረዉን ኳስ ቢኒያም ፍቅሬ ወደ ግብነት ቀይሮ ዲቻዎችን መሪ ማድረግ ችሏል።

ከዕረፍት መልስ ተሻሽለዉ የተመለሱት ሻሸመኔ ከተማዎች በቶሎ የአቻነት ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም በ52ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከአብዱልቃድር ናስር የተቀበለዉን ኳስ አዲሱ ፈራሚ ስንታየሁ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል። ከመጀመሪያው አጋማሽ ይልቅ መቀዛቀዝ የታየባቸዉ ዲቻዎች በአጋማሹ በ63ተኛዉ ደቂቃ ላይ በቢኒያም ፍቅሬ አማካኝነት ከርቀት ተጠቃሽ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ።

በሙከራም በጨዋታ እንቅስቃሴም ረገድ የተሻሉ የነበሩት ሻሸመኔዎች በ73ተኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል ፤ በዚህም ሀብታሙ ንጉሴ ከቅጣት ምት ያሻማዉን ኳስ አሸናፊ ጥሩነህ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን ሻሸመኔ አሸናፊ ማድረግ ችሏል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ሀድያ ሆሳዕና የሊጉን መሪ መቻል ሲያሸንፍ ፤ ፋሲል ከነማም ከመመራት ተነስቶ ወሳኝ ድል አሳክቷል !!
Next Article ቡናማዎቹ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሲዳማ ቡናን ሲያሸንፉ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ዳግም የሊጉን መሪ መሆን የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችየአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

” ከዋሊያዎቹ ጋር ያደረግነው የሜዳችን ጨዋታ ማሸነፍ አይገባንም ነበር ” ሀሚዱ ጂብሪላ የኒጀር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 5 years ago
ኢትዮጵያ ነገ ተጋጣሚዋን ታውቃለች
የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 11ኛሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ 
ተክለማርያም ሻንቆ የገብረመድህን ሃይሌ ስብስብን ለመቀላቀል ተስማምቷል !
በረከት ደስታ በሰርግ ምክንያት ከዋሊያዎቹ ተሰናብቷል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?