By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ቡናማዎቹ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሲዳማ ቡናን ሲያሸንፉ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ዳግም የሊጉን መሪ መሆን የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችኢትዮጵያ ንግድ ባንክሲዳማ ቡናአዳማ ከተማየጨዋታ ዘገባየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቡናማዎቹ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሲዳማ ቡናን ሲያሸንፉ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ዳግም የሊጉን መሪ መሆን የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

– ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን ከድንቅ የጨዋታ ብልጫ ጋር ማሸነፍ ችሏል ።

ቀን 10 ሰዓት ሲል በጀመረዉ የ16ተኛዉ ሳምንት የመጨረሻ ዕለት ጨዋታ ድንቅ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የተመለከትን ሲሆን በሙከራ ረገድ ግን ቡናዎቹ የተሻሉ ሁነዉ ተስተዉሏል ፤ በዚህም ገና በመባቻዉ በ9ነኛዉ ደቂቃ ላይ አንተነህ ተፈራ ከመስፍን ታፈሰ የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ ተከላካዩ ደስታ ዮሐንስ አውጥቶበታል። የጨዋታዉን የበላይነት መቆጣጠር የቻሉት ቡናማዎቹ ምንም እንኳን እንደነበራቸዉ ብልጫ ሙከራን ማድረግ ባይችሉም ከደቂቃዎች በኋላ በአብዱልከሪም ወርቁ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ለጥቂት ወጥታለች ።

በአንፃሩ ቡናማዎቹ ትተዋቸዉ የሚሄዱ ክፍት ቦታዎችን ለመጠቀም ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች አንድ ሁለት ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም ኢላማቸዉን ሳይጠብቁ ወጥተዉባቸዋል። ከዕረፍት መልስ የበላይነታቸዉን አጠናክረዉ የቀጠሉት ቡናማዎቹ በመስፍን ታፈሰ እና በፍቃዱ አለማየሁ አማካኝነት ከመስመር በተነሱ ኳሶች ድንቅ ሙከራዎች ማድረግ ችለዋል።

- ማሰታውቂያ -

አሁንም ተደጋጋሚ ሚከራዎችን ማድረግ የቀጠሉት ቡናማዎቹ በ63ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም አስራት ያቀበለዉን ኳስ አብዱልከሪም ወደ ግብ ሲሞክር ኳሷ የጊት ጋትን እግር ነክታ ወደ ግብ ተቀይራለች። ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ በ66ተኛዉ ደቂቃ ላይ በዳመነ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችለዉ የነበሩት ሲዳማዎች ዳግም ግብ ተቆጥሮባቸዋል። በዚህም በ74ተኛዉ ደቂቃ ላይ አብዱልከሪም ከብሩክ በየነ የተቀበለዉን ሰንጣቂ ኳስ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። በመጨረሻም በጨዋታው የበላይ የነበሩት ቡናማዎቹ በ85ተኛዉ ደቂቃ ላይ በዕለቱ ኮከብ የነበረዉ መስፍን ለብሩክ ያቀበለዉን ኳስ አጥቂዉ ወደ ግብነት ቀይሮ ጨዋታዉ በቡና 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

– በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳግም የሊጉ መሪ መሆን የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል ።

በሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ እንቅስቃሴ ገና በመባቻዉ በ3ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ተቆጥሮበታል። በዚህም ባሲሩ ዑመር ያቀበለዉን ኳስ የመስመር አጥቂዉ ኪቲካ ጀማ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን ገና በመባቻዉ መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ ግደይ እና ቢኒያም ጌታቸው አማካኝነት እጅግ አስቆጭ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።

በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ተደጋጋሚ ጫና የተደረገባቸዉ እና ግብም የተቆጠረባቸዉ አዳማ ከተማዎች በ22ተኛዉ ደቂቃ ላይ የአቻነት ግብ አጊኝተዋል ። በዚህም የመስመር አጥቂዉ ቢኒያም አይተን ያቀበለዉን ኳስ ዮሴፍ ታረቀኝ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል። የአቻነት ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ ዳግም ግብ ለማስቆጠር መጫወት የቀጠሉት ባንኮች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ አጋማሹ ሊጠናቀቅ ሲል ዳግም መሪ የሆኑበትን ግብ አስቆጥረዋል ። በዚህም ከቀኝ በኩል የተሻማዉን ኳስ አጥቂዉ በረከት ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቦቹ ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ከዕረፍት መልስ እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ የጨዋታውን ብልጫ መዉሰድ የቻሉት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ከደቂቃዎች በኋላ በ63ተኛዉ ደቂቃ ላይ መሪነታቸዉን ወደ 3ለ1 ከፍ ያደረጉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም አጥቂዉ ቢኒያም ጌታቸዉ ከባንክ የቀኝ ማጥቃት በኩል ያገኘዉን ኳስ በቶሎ ወደ ግብ በመላክ ግቡን ለቆ ወጥቶ የነበረዉ ሰይድ ሀብታሙ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

በጨዋታው የመጨረሻው ደቂቃዎች ላይ በተደጋጋሚ አደጋዎችን ለመፍጠር ጥረት ሲያርጉ የነበሩት አዳማ ከተማዎች እንደ ልፋታቸው ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ፤ በተቃራኒው አራተኛ ግብ ተቀይሮ በገባዉ ሳይመን ፒተር አማካኝነት ተቆጥሮባቸዉ መርሐግብሩ ፍፃሜዉን አጊኝቷል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሻሸመኔ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል !!
Next Article ተመስገን ዳና የአዲስ አዳጊዉ ክለብ አሰልጣኝነት ሆኗል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
Uncategorized

ቶታል አፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ /LIVESCORE/

hatricksport team By hatricksport team 9 years ago
ባህርዳር ከተማ ሀሪስተን ሄሱን አስፈርሟል።
ሀድያ ሆሳዕና የአንድ ተጫዋችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የነባር ተጫዋቹንም ዉል አድሷል !!
ሪፖርት | ሰበታ ከተማና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርተዋል
“ከ40 እስከ 50 ሺህ ዶላር የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚሸፍንልን ይሆናል” “በቀጣይ አምስት ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሀገሩና በደጋፊው ፊት መጫወት የሚችልበት ዕድል አለው…..” አቶ ባህሩ ጥላሁን ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?