በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እየተመሩ በዝውውር ገበያዉ ላይ በንቃት በመንቀሳቀስ የተከላካዩን ያሬድ ባየ እና የመስመር ተጫዋቹን ዱሬሳ ሹቤሳ ዝዉዉር ያጠናቀቁት ባህርዳር ከተማዎች አሁን ደግሞ የመስመር ተጫዋቹን ፍፁም ጥላሁንን ሶስተኛ ፈራሚ በማድረግ ወደ ቡድናቸዉ ተቀላቅለዋል።
ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ቡና እና ከፋ ቡና እንዲሁም ያለፉትን ሁለት አመታት ለአዲስ አበባ ከተማ መጫወት የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ቀጣዩቹን ሁለት አመታት ለጣና ሞገዶቹ ለመጫወት ፊርማዉን ማኖሩ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ