ሉሲዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ይረዳቸዉ ዘንድ ሁለተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታቸውን በዛሬዉ ዕለት ያደርጋሉ !!

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከፊታቸዉ ለሚጠብቋቸዉ የማጣሪያ ጨዋታ ሉሲዎቹ ልምምዳቸውን በካፍ የልህቀት ማዕከል በመስራት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የመጀመሪያ የማጣርያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ በሴንት ሜሪ ስታዲየም ካምፓላ ላይ ጥቅምት 10 የሚያካሂዱት ሉሲዎች በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ 15 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር ከቀኑ 9:30 ላይ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።

 

ከሳምንት በፊት ጨዋታቸዉን በዚያዉ በካፍ አካዳሚ አከናዉነዉ በነበረዉ የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ሉሲዎቹ ሴናፍ ዋቁማ እና ስራ ይርዳው ጎሎች ታግዘዉ 2ለ0 ማሸነፋቸዉ ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከመስከረም 15 ጀምሮ በካፍ የልህቀት ማዕከል በቀን ሁለት ጊዜ በአካል ብቃት እንዲሁም በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ዝግጅታቸውን ሲከዉኑ የቆዩ ሲሆን ፤ ከትላንት ጀምሮ ደግሞ ልምምዳቸውን በቀን ወደ አንድ ጊዜ በመቀነስ ለዛሬው የአቋም መለኪያ ጨዋታ መዘጋጀታቸውን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *