መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለቱ የሸገር ክለቦች መካከል በተደረገዉ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ፈረሰኞቹ አሸንፈዋል !!
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

በሁለቱ የሸገር ክለቦች መካከል በተደረገዉ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ፈረሰኞቹ አሸንፈዋል !!

አጋራ
አጋራ

በቅድመ ዉድድር ዝግጅት ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ረፋድ 4:00 ሰዓት ላይ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ቢሾፍቱ ላይ አድርገዋል።

ከሁሉም ክለቦች አስቀድሞ ዝግጅቱን በቢሾፍቱ የጀመረዉ እና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ተሳታፊ የሆነዉ የካሳየ አራጌ ስብስብ በዛሬው ዕለት ከሌላኛው የመዲናዉ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገዉ የአቋም መለኪያ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 በሆነ ዉጤት ተሸንፏል።

በዛሬዉ ጨዋታ በሁለቱም ክለቦች በኩል ወሳኝ የሚባሉ ተጫዋቾቻቸውን ለብሔራዊ ቡድን በማስመረጣቸዉ ምክንያት በአብዛኛዉ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝዉዉር መስኮት ክለቦቹን የተቀላቀሉ እንዲሁም በቅድመ ዉድድር ዝግጅቱ ላይ እየተተሳተፉ የሚገኙ ተጫዋቾችን አስለፈዉ ለመጫወት ችለዋል።

የሀገሪቱ የከፍተኛ ሊግ እርከን (ፕሪሚየር ሊግ) ክለቦች ለ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዉድድር ለመዘጋጀት የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን እንደጀመሩ ይታወቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...