መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የጨረታ ማስታወቂያ አዉጥቷል !!
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የጨረታ ማስታወቂያ አዉጥቷል !!

አጋራ
አጋራ

ከቀጣዩ የ2014 የዉድድር አመት አንስቶ በሚካሄዱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ከስታዲየሙ የመያዝ አቅም 25% የሚሆኑ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ገብተዉ ጨዋታዎችን እንዲታደሙ መወሰኑ ይታወቃል። ከዚህ ጋር ተያይዞም አክሲዮን ማህበሩ የትኬት መቁረጫ መንገዶችን በተመለከተ ጨረታ አዉጥቷል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/ማ በ2014 የዉድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የሚያደርጉትን 240 ጨዋታዎች ከእግርኳስ ስፖርት ተመልካቾች የሚሰበሰብ የትኬት ሽያጭን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ መሰብሰብ እንደሚፈልግ አክሲዮን ማህበሩ ያወጣው ማስታወቂያ ይጠቁማል።

በመሆኑም ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከጳጉሜ 2/2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 7/2014 ዓ.ም ድረስ በፕርሚየር ሊጉ ቢሮ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ አጠገብ ሜይስዊ ህንፃ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 በመክፈል መዉሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ጨረታዉም አርብ መስከረም 7/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።

በተጨማሪም የጨረታ ተሳታፊዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ሲል አክሲዮን ማህበሩ የገለፀ ሲሆን ሰነዶቹም የሚከተሉት ናቸዉ:-

–የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣
-የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፣
-የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣
-በመንግሥት ግዥዎች ኤጀንሲ መወዳደር የሚችል መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት።

በመጨረሻም ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ይጠቁማል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...