By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Reading: የአመቱ ኮከብ ተመራጮች የሽልማት ገንዘብ አለመከፈሉ አነጋጋሪ ሆኗል
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
Š 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የአመቱ ኮከብ ተመራጮች የሽልማት ገንዘብ አለመከፈሉ አነጋጋሪ ሆኗል

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

👉 የቀጥታ ስርጭቱን የሚቀርጹት የካሜራ ባለሙያዎች የሁለት ደመወዝ አልተከፈለም ተባለ….

በ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሳዩት ምርጥ አቋም የአመቱ ኮከቦች ተብለው የተመረጡ ስፖርተኞች የሽልማት ክፍያ አለመፈጸሙ አነጋጋሪ ሆኗል።

በ2015 የአመቱ ኮከብ ተብለው ለተመረጡ 3 ተጨዋቾች ፣ 2 አርቢትሮችና 1 አሰልጣኝ መከፈል የነበረበት ወደ 920 ሺህ ብር የሽልማት ክፍያ አለመፈጸሙ ታውቋል። በሀያት ሪጀንሲው ፕሮግራም የአመቱ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ የተመረጠው
የቅ/ጊዮርጊሱ ቢኒያም በላይ 210 ሺህ ብር፣ በአመቱ ኮከብ አሰልጣኝነት የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ 200 ሺህ ብር ፣ በአመቱ ተስፈኛ ተጫዋችነት የአዳማ ከተማው ዮሴፍ ታረቀኝ 150 ሺህ ብር ፣ በአመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂነት የኢትዮጵያ መድኑ አቡበከር ኑራ 150 ሺህ ብር ፣ በአመቱ ኮከብ አርቢትርነት ፌዴራል ዳኛ ቢኒያም ወ/አገኘሁ 105 ሺህ ብር እንዲሁም በኮከብ ረዳት አርቢትርነት ኢንተርናሽናል ረዳት አርቢትር ትግል ግዛው 105 ሺህ ብር ቃል ቢገባም የነኚህን ወደ 1 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ክፍያ ሳይከፍል መቆየቱ ጥያቄ አስነስቷል።

ከዚሁ የአመቱ ኮከቦችን ሽልማት ሳንወጣ ሽልማቱን የሚሸልመው ተቋም ማነው የሚለው አነጋጋሪ ሲሆን ከፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር በተገኘ መረጃ ሱፐር ስፖርት የስያሜ መብቱንና የኮከብ ሽልማቱን የሚሸፍን ሲሆን አክሲዮን ማህበሩ በኮከቦች ሽልማት ላይ ምንም አይነት የገንዘብ አስተዋጽኦ አድርጎ እንደማያውቅ ተገልጿል። ባለፉት አመታት የስያሜ መብቱን የወሰደው ቤትኪንግ ይከፍል እንደነበረና የ2015ቱን ሽልማት
ከሱፐር ስፖርት እንደሚጠበቅ ታውቋል።

- ማሰታውቂያ -

የክፍያው ጉዳይ አነጋጋሪ ያደረገው ከ10 የማያንሱ ካሜራማኖች የሁለት ወር ደመወዝ አለመከፈሉ ነው። ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ሙሉ ፕሮዳክሽኑን የያዘው የኬንያው ተቋም ላይቭአይ ውሉ ተሰርዞ ከኢትዮጵያ ወጥቷል። ዲ ኤስ ቲቪ በውሉ መሠረት ለተቋሙ ሙሉ የሚጠበቅበትን ሂሳብ የከፈለ ቢሆንም ላይቭአይ ግን የሰራተኞቹን ደመወዝ ባለመክፈሉ እንዲከፍል ተደጋጋሚ ጊዜ ሲጠየቅ መቆየቱና አምና ከአማራ ቲቪ ጋር በነበረው ግንኙነት ከፍተኛ ሂሳብ በማውጣቱ ተቋሙ ላይ ችግር መፈጠሩ ታውቋል። ዲ ኤስ ቲቪ ሳተላይትና ሚክሰር በማምጣት በአማራ ቲቪ የተጠቀመ ሲሆን ላይቭ አይ መክፈል ባለመቻሉ ዲ ኤስ ቲቪ ከፍሎ ከተቋሙ ጋር ሂሳቡን ማወራረዱ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ያም ሆኖ ዲ ኤስ ቲቪ ከሰራተኞቹ ጋር ምንም አይነት የውል ስምምነት ባይኖረውም ሰራተኞቹ ላይ ባየው ዲሲፕሊንና የስራ ታታሪነት ክፍያቸውን በመክፈል በውል ስምምነቱ መሠረት ከኬንያው ላይቭ አይ ጋር ለመነጋገር ወስኖ ክፍያውን ለመክፈል እየሰራ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከዲ ኤስ ቲቪ የኢትዮጵያ አንድ የስራ አመራር በተገኘ መረጃ የካሜራ ባለሙያዎችና የኮከቦቹ ሽልማት የክፍያ ሂደት እየተከናወነ በመሆኑ ክፍያው በቀጣዮቹ ጊዜያት የሚፈጸም ይሆናል ተብሏል። ኤኚሁ አመራር ሱፐር ስፖርት በውሉ መሠረት 5 አመቱን እንደሚፈጽም አረጋግጠው የስያሜ መብቱን ከሚገዛው ተቋም ጋር ለመፈራረም ቀገሮ መያዙ የዲ ኤስ ቲቪን መቆየቷ የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ዲ .ኤስ. ቲቪ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 235 ጨዋታዎች መሃል 180 ጨዋታዎችን እንደሚያሰተላልፍ ይፋ ሆኗል። ከፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበሩ ጋር ጠንካራ ግንኙነት የፈጠረው ዲ ኤስ ቲቪ በገበያው ያገኘው ተቀባይነትና ስፖርት ቤተሰቡ ላይ ባየው ፍላጎትት ውሉ ከሚያስገድደው በላይ ጨዋታዎችን እያስተላለፈ መሆኑ ታውቋል። የሊጉ አክሲዮን ማህበርና ዲ ኤስ ቲቪ የቅርብ ምንጮች በተገኘ መረጃ ዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ በጀመረበት 2013 ፕሪሚየር ሊጉ በ13 ክለቦች ሲካሄድ የነበረው ጨዋታ 156 ነበር ከዚህ የጨዋታ ብዛት በውሉ አስገዳጅ የሆነው 60 ጨዋታ ብቻ ቢሆንም የተላለፈው 154ቱ ጨዋታ ነው። በሁለተኛው ዓመት በ2014 ደግሞ የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ቁጥር 16 ሲሆን በአመቱ 240 ሲሆን በውሉ መሠረት 120 ጨዋታ ተጠብቆ የተላለፈው 235 እንደነበር ታውቋል።

በሶስተኛው አመት በ2015 ይተላለፉ ከነበሩት 240 ጨዋታዎች 160ዎቹ አስገዳጅ ሆነው የተላለፈው 167 ጨዋታ መሆኑ ተረጋግጧል። የአራተኛው ዓመት የ2016 መርሃግብር መስከረም 20/2016 የተጀመረ ሲሆን አመቱ ሲጠናቀቅ በውል ስምምነቱ መሠረት እንደተቀመጠው 180 ጨዋታ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል። የዘንድሮው የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ጠንካራ አቅምና አስፈላጊ የሆኑ የፕሮዳክሽን መሳሪያዎች ከተሟላለት ኦ.ቢ ኤን ጋር በመነጋገር የመጀመሪያ ሳምንት የሊጉን 8 ጨዋታዎች ያስተላለፈው ዲ ኤስ ቲቪ በፊፋ ካላንደር መሠረት የአለም ሀገራትን የማጣሪያና የወዳጅነት ጨዋታ በማስተላለፉ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዲ ኤስ ቲቩ ሳይተላለፉ ቀርተዋል። ለዚህ ደግሞ በርካታ መላምቶች እየተሰጡ ቢሆንም ከሊግ ኩባንያው በተገኘ ዲ ኤስ ቲቪ ጨዋታዎቹ እንዳይተላለፉ ፊፋ ባስቀመጠው ካላንደር መሠረት እንዲዘለሉ ቢጠይቅም የብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ ስላለና ስለሚቋረጥ ሊጉ በጊዜ መጠናቀቅ አለበት በሚል ውሳኔ ጨዋታዎቹ እንዲቀጥሉ መደረጉን ገልጸዋል። ሶስተኛው ሳምንትና አራተኛው ሳምንቶች የቀጥታ ስርጭት እንደሌለና በቀጣዮቹ ሳምንታት ግን ስርጭቱ ተስተካክሎ እንደሚቀጥል ከታማኝ ምንጭ የተገኘው ማስረጃ ያስረዳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፕሪሚየር ሊጉ ስያሜን ገዝቶ የነበረው ቤትኪንግ ከስሬያለሁ በሚል አቋርጦ ከወጣ በኋላ የሊጉን ስያሜ መብት የወሰደ ተቋም አልተገኘም። ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ምንጮች በተገኘ መረጃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ300 ሚሊዮን ብር የሁለት አመት ውል ፈርሞ ሊጉ የኢትዮጵያና ንግድ ባንክ ፕሪሚየር ሊግ ሊባል ነው ቢባልም እስካሁንም የተረጋገጠ ነገር ከተቋማቱ አልወጣም። በሁለቱ ወገኖች መሃል ድርድሩ እየተካሄደ እንደሆነና የወረቀት ጉዳዮች ብቻ እንደቀረ እየተነገረ ነው ከቀናት በፊት ይፋ በሆነ መረጃ ደግሞ የሊጉን ስያሜ የገዛውን ተቋም ለማሳወቅና የፊርማ ስምምነቱን ለመፈጸም ለፊታችን ማክሰኞ 8 ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠርቷል።

በዶክተር ወገኔ ዋልታንጉስ የሚመራው የሊግ ኩባንያው የውድድር ኮሚቴ ባወጣው አዲሱ መርሃግብር መሠረት አራተኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር የፊታችን ረቡዕ ጀምሮ በአዳማው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሚቀጥል ይሆናል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article ኢትዮጵያ ቡናና ቤቲካ ኢትዮጵያ ውላቸውን አራዘሙ
Next Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ካፍ ኮንፌዴሬሽን ካኘ መከላከያ ከ ያንግ ስፖርትስ አካዳሚ /LIVESCORE/ በቀጥታ

hatricksport team By hatricksport team 9 years ago
“መልክህ አላማረኝም ብለው የተነሱ ደጋፊዎች ቢኖሩም ሁሉንም
በውጤት ለማሳመን ጠንክሬ እየሰራሁ ነው”አሰልጣኝ ስዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)
የጨዋታ ዘገባ| ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ድልን ተቀዳጀ
ሄኖክ ሀሰን፣ ብሩክ ማርቆስ እና አሰልጣኝ አትክልቲ በርሃ የጨዋታ እገዳ ሲጣልባቸው እንዲሁም ከክለብ ድሬደዋ ከተማ ቅጣት ተላልፎበታል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 3ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

Š Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?