የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 12 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አራቱ በመሸናነፍ ቀሪ አራቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ 17 ጎሎች በ16 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 34 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም ።
ክለቦች ላይ በተላለፉ ውሳኔዎች ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ3 ኛ ሳምንት ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከባህርዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኞችን እና የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋችን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበት የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ክለቡ ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
በተጨማሪም ለሻሸመኔ ከተማ የቡድን መሪ እና ዋና አሰልጣኙ አቶ ፀጋዬ ወንድሙ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሊያነጋግራቸው ጥሪውን አስተላልፏል ::