የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የክፍያ ጣሪያ በተመለከተ ሊደረግ የነበረው ስብሰባ ተራዘመ።
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ከሁለት አመት በፊት ክለቦች በተገደበ የክፍያ ጣሪያ ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል በሚል ከሁለት በአመት በፊት የተጫዋቾች የክፍያ ጣሪያ በሚል ህግ ፀድቆ አንድ ክለብ በአንድ አመት ውስጥ መጠቀም አለበት ተብሎ አስቀድሞ 56 ሚሊዮን በመቀጠል ደግሞ 70 ሚሊዮን ብር ሊያወጣው የሚችለው በጀት ነው ተብሎ ውሳኔ ተሰጥቶበት ወደ ስራ ቢገባም ከአፈፃፀም አኳያ ግን በርካታ ክለቦች ህጉን ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ ከጀርባ በሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮች ገሚሱን ጠቃሚ ህግ አክባሪውን ደግሞ የሚጎዱ ተግባራት ሲፈፀሙ አስተውለናል።

ህጉ ቢወጣም ተግባራዊ ባለመሆኑ አክብረን እየሰራን ያለነውን ክለቦች እየጎዳ ነው የሚባልለት ይህ የክፍያ ጣሪያ ስርዓትን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለማንሳት አልያም የገንዘብ መጠኑን ከፍ ለማድረግ ከክለቦች ጋር ውይይት ለማድረግ ለሐምሌ 19 ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ቀኑ ተገፍቶ ሐምሌ 23/2018 እንዲሆን አክሲዮን ማህበሩ መወሰኑን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየት ይስጡ