በአልጄሪያ ሊግ 1 ጎል ያስቆጠረውን አጥቂ ወላይታ ድቻ ሊያስፈርም ነው።

ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ቡድናቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች የውጪ ዜግነት ያላቸውን አጥቂዎች ለማስፈረም ሰሞኑን እየመለከተ የሚገኝ ሲሆን ጋናዊ አጥቂ ለማስፈረም ጥረት አድርጎ ባለመሳካቱ ወደ ናይጄሪያዊው አጥቂ ፊቱን ያዞረ ይመስላል። የናይጄሪያ ዜግነት ያለው ዮሱፍ ሳውራ ምንአልባትም ክለቡን ሊቀላቀል እንደሆነ ተሰምቷል።
ዊኪ ቱሪስትስ ከተባለው የሀገሩ ክለብ በተጨማሪ ለናሳሪዋ ዩናይትድ በሁለት አጋጣሚዎች ያገለገለው እና በ2024/25 የናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ 18 ጎሎችን በማስቆጠር የአመቱ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ የቋጨው እና በዘንድሮው የ2026 የውድድር ዘመን ግን ወደ አልጄሪያ የሊግ ዋኑ ክለብ ጄ ኤስ ሳውራን ቢቀላቀልም በ10 ጨዋታ 1 ጎል ብቻ ያስቆጠረው ይህ አጥቂ ቀጣይ መዳረሻው ወላይታ ድቻ ሊሆን መቃረቡ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ