ኢትዮጵያ ቡና በመጨረሻም የሦስቱን ተጫዋቾች ውል ዛሬ አራዘመ።
ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለመቀጠል እና ላለመቀጠል በሁለት መልክ ሲጓዙ የነበሩት እና ወደ ሌላ ክለብ ሊያመሩ የነበሩት ሦስት ተጫዋቾች በመጨረሻም በዛሬው ዕለት በይፋ ለኢትዮጵያ ቡና ፈርመዋል።

በኢትዮጵያ ቡና ያለፉትን አራት አመታት አስደናቂ ብቃታቸውን ሲያሳዩን የነበሩት እና የኢትዮጵያ ቡና የወጣት ቡድን ፍሬ የሆኑት አማካዮቹ ይታገሱ ታሪኩ እና ኤርሚያስ ሹምበዛ እንዲሁም ደግሞ አጥቂው አማኑኤል አድማሱ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ቡና የሚያቆያቸውን የሁለት አመት ውል በዛሬው ዕለት መፈራረማቸውን አረጋግጫለሁ።
አስተያየት ይስጡ