By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Reading: የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ል ሃላፊ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢኒያም ምሩጽን እንዲታገድ ሜድረጉ ቅሬታ ቀሰቀሰ
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሲዳማ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
Š 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችቃለመጠይቅአትሌቲክስ

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ል ሃላፊ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢኒያም ምሩጽን እንዲታገድ ሜድረጉ ቅሬታ ቀሰቀሰ

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

 

👉 …..የአዲሰ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ
ጉባኤም ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ …

👉 “ባሳየነው ለውጥ አንደኛ ተብዬ መሸለም እንጂ እንዲህ መገፋትን አልጠበኩም በጣም ቅር ነው ያለኝ”

👉 “መብትቴን የጣሱትን ግለሰቦች ላይ ህጋዊ ርምጃ እወስዳለሁ”

- ማሰታውቂያ -

አቶ ቢኒያም ምሩጽ
/ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፊዴሬሽን ፕሬዝዳንት/

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1994 የወጣው የዲያስፖራ አዋጅ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከመከላከያ፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት እንዲሁም ከመምረጥ መመረጥ ውጪ ሌሎቹን እንዲሰሩ ይፈቅዳል… የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ግን ይህን የተቀበለው አይመስልም …. የካናዳ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ቢኒያም ምሩጽ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይካፈል የቢሮው አመራሮች ጣልቃ መግባታቸው አቶ ቢኒያም ምሩጽን ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲወስደው አድርጎታል… የቢሮው
ም/ል ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የአቶ ቢኒያምን ውክልና በስልክ ትዕዛዝ ሲያሽሩ ጉዳዩ ያልጣማቸውና አለመግባባቱን ከውጪ ሲመጡ የሰሙት የቢሮው ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ደግም ጉዳዩን ላጣራ በሚል
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሊያካሂደው የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤና የምርጫ ቀን እንዲራዘም አድርገዋል.. /የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዚህም ውጪ ከ32ቱ ፌዴሬሽኖች መሃል በአንዱ ፌዴሬሽን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና አላሰራ በሚል ውስጥ ለውስጥ የቆረቆዘ ውዝግብ ውስጥ የገባ ሲሆንዘ ሙሉ ማስረጃ እጃችን እንደገባ የምናቀርበው ይሆናል../ ለዛሬ ግን አቶ ቢኒያም ከአቶ ዳዊት ጋር የገቡበትን ውዝግብ በተመለከተ ከጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያደረጉት ቃለምምልስን አቅርበንላቸዋል….

ሀትሪክ:- የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ መወዳደር አትችልም ለማለት ያቀረቡት ምክንያት ምንድነው…?

ቢኒያም:- ዋናው ምክንያትማ የውጪ ሀገር ዜጋ ነህ ፕሬዝዳንታዊ ውድድር ላይ መካፈል አትችልም በሚል ነው… የዛሬ አራት አመትም የተወዳደርኩት የውጪ ሀገር ዜጋ ሆኜ ነው ምንም የተፈጠረ ነገር በሌለበት ለምን ሊከለክሉ እንደፈለጉም አልገባኝም… በምን መንገድ እንዳልወዳደር ለማድረግ እንደፈለጉም አልገባኝም…

ሀትሪክ :- በርግጥ ግን መወዳደር የሚከለክል ህግ አለ….?

ቢኒያም:- ኧረ በፍጹም የለም …በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1994 የወጣ የዲያስፖራው አዋጅ ላይ በግልጽ ተቀምጧል ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከመከላከያ፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት እንዲሁም ከመምረጥ መመረጥ ውጪ ሌሎቹን እንዲሰሩ ይፈቅዳል። አዋጁ ነጋሪት ጋዜጣ ላይ የወጣ ነው ብዬ ወስጄ ሰጥቻቸዋለሁ እንግዲህ ምን እንደሚሆን አብረን የምናየው ነው የሚሆነው.. የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለክልል ፌዴሬሽኖች እንደማያገባቸው በገለጸበት ሂደት ነው አትወዳደርም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነህ ብለው ሊከለክሉኝ የፈለጉት …

ሀትሪክ:- ትዕዛዙን ያስተላለፈው ማነው…?

ቢኒያም:- የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊው አቶ ዳዊት ትርፉ ናቸው…. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድሬ ያሸነፍኩትና የተወከልኩት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነው የጽ/ቤት ሃላፊው ጋር ደውሎ ለላከው ውክልና ሌላ የመሻሪያ ደብዳቤ ጻፍ ብሎ ያጻፈው እሱ ነው ሃላፊውም በደብዳቤ ሳይሆን በስልክ ተነግሮት ነው የጻፈው… አሁን የመሻሪያ ደብዳቤ ተጽፏል።

ሀትሪክ:- ጉባኤው ዘገየ የሚለው ነገርስ…?

ቢኒያም:- የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊው አቶ በላይ ደጀን ከሀገር ውጪ ስለነበር ሲመለስ ሰምቶ ቢሮው ጣልቃ መግባት የለበትም እንዲህ አይነት አሰራር የለም ማጣራት እናደርጋለን በሚል ጥቅምት 11/2016
ሊካሄድ የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲዘገይ አድርጎታል …

ሀትሪክ:- ጉባኤውን አራዝሙ የሚል ደብዳቤ
ደርሷችኋል ..?

ቢኒያም:- ጉባኤው እንዲራዘም የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊው አቶ በላይ ደጀን ነው ያዘዘው …በርግጥ እንዲራዘም የሚያዝ ደብዳቤ አልደረሰንም …በቀጣይ በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ደረጃ ቢሮው ህጋዊ ደብዳቤ እንዲሰጠን እንጠይቃለን …

ሀትሪክ:-ጉዳዩን ወደ ህግ ወሰድከው የሚልም መረጃ ሰምቻለሁ… እውነት ነው..?

ቢኒያም:- አዎ ግለሰቦችን ነው የምከሰው … በመንግስት በተወካዮች ምክር ቤት የተፈቀደውን መብቴን ለመጣስ የምከሩትን ግለሰቦችን ነው ፍርድ ቤት የማቆመው …

ሀትሪክ:- የአራት አመቱ ፕሬዝዳንታዊ ቆይታህ እንዴት ይገለጻል..?

ቢኒያም:- የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ከአራት አመት በፊት የምታውቀው ይመስለኛል..እንዳሁኑ አልነበረም የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት ሶስት አመታት በተከታታይ ባደረገው ግምገማ ከ32 ፌዴሬሽኖች በስራ አፈጻጸም አንደኛ ተብሎ የተመረጠው የኛ የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው .. ..ከፕሮጀክት ፣ከውድድር ፣ ከቢሮ አደረጃጀት አንጻር ባሳየነው ለውጥ አንደኛ ተብዬ መሸለም እንጂ እንዲህ መገፋትን አልጠበኩም በጣም ቅር ነው ያለኝ . … ፌዴሬሽኑን ላገለግል ስለመጣሁ ባለፉት አራት አመታት እንደ ፕሬዝዳንትነቴ አንድም ቀን አበል ወስጄ አላውቅም የነዳጅ ተሰጥቶኝ አያውቅ…በነጻ አገለገልኩ እንጂ አምስት ሳንቲም ወስጄ አላውቅም…. በራሴ መኪና 42 ኪሎ ሜትር እየለካሁ የሰራሁ ሰው ነኝ ምን አድርጌያቸው እንደሆነም አላውቅም በጣም ቅር ብሎኛል በህግ መብቴን ለማስከበር ግን ጉዳዩን ወደ ህግ እወስደዋለሁ…

ሀትሪክ :- አመሰግናለሁ አቶ ቢኒያም ….

ቢኒያም:- እኔም አመሰግናለሁ..

ማሳሰቢያ:-
ከአቶ ቢኒያም ምሩጽ ጋር በተደረገው ቃለምምልልስ ዙሪያ ቢሮው ምላሽ ካለው ለማስተናገድ በራችን ክፍት መሆኑን እንገልጻለን…..

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ
Next Article ኢትዮጵያዊቷ ቡዜ ድሪባ የቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን አሸናፊ ሆነች

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችመከላከያየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወላይታ ድቻ

የጨዋታ ዘገባ | ወላይታ ድቻ ወደ መሪዎቹ የቀረበበትን ድል አስመዝግቧል

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 4 years ago
ሀዋሳ ከተማ አማካኝ ለማስፈረም ተስማማ !
ሀዋሳ ከተማ የቀድሞዉን የፈረሰኞቹ የግብ ዘብ አስፈርሟል !!
ሲዳማ ቡና መደበኛ ልምምዱን በቴሌግራም ጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ሀ የመጨረሻ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተካሂደዋል ።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

Š Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?