መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ የጣና ሞገዶቹ ከሁለት ተጫዋቾቻቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል !
ባህርዳር ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

የጣና ሞገዶቹ ከሁለት ተጫዋቾቻቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል !

አጋራ
አጋራ

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን ከቀጠሩ በኋላ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ አሁን ደግሞ ከሁለቱ ተጫዋቾቻቸው ወሰኑ አሊ እና ሚኪያስ ግርማ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ዕርግጥ ሆኖአል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን ተጫዋች የነበረዉ የመስመር አጥቂዉ ወሰኑ አሊ ባህር ዳር ከተማ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ የስብስቡ አባል እንደነበረ ይታወቃል። ከ2011 የዉድድር አመት አንስቶ ከባህርዳር ከተማ ጋር በፕሪምየር ሊጉ መቆየት የቻለዉ ተጫዋቹ ከአራት አመታት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተረጋግጧል።

ሌላኛው ከክለቡ ጋር የተለያየዉ ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሚኪያስ ግርማ መሆኑ ታዉቋል ። የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ አራዳ ክ/ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች የነበረዉ ተከላካዩ እንደ ክለብ አጋሩ ወሰኑ አሊ ሁሉ እርሱም ከ አራት አመታት የባህርዳር ቆይታ በኋላ ከጣና ሞገዶቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል ። ተጫዋቾች ከባህርዳር ከተማ  ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ተከተሎ በቀጣይ ቀናቶች ወደ ሌሎች ክለቦች ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...