በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት እስከመጨረሻዎቹ ሳምንታት ድረስ ላለመውረድ ሲታገል የነበረው ባህርዳር ከተማ በዝውውር መስኮቱ ነቃ ብለው እየተሳተፉ ካሉ ክለቦች አንዱ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ሀብታሙ ታደሰን አራተኛ ተጫዋች በማድረግ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ።
ተጫዋቹ በውድድር ዓመቱ በሙሉጌታ ምህረት በሚመራው ሀድያ ሆሳዕና ጥሩ ብቃትን ሲያሳይ የቆየ ሲሆን ባደረጋቸው 25 ጨዋታዎችም 8 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።
የጣና ሞገዶቹ ከዚህ ቀደም ያሬድ ባየህ ፣ ዱሬሳ ሹቢሳ እና ፍፁም ጥላሁንን ማስፈረማቸው ይታወሳል ።