መነሻ ገጽ Africa ተጠባቂዉን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ እንደሚመራው ታዉቋል
AfricaCameron 2022አፍሪካአፍሪካ ዋንጫዜናዎች

ተጠባቂዉን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ እንደሚመራው ታዉቋል

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከጥር 1/2014 ዓ.ም በካሜሩን በተጀመረው የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያን ከወከሉ ባለሙያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።

ከባምላክ ተሰማ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በአፍሪካ ዋንጫዉ ቴክኒክ ክፍሉ እየሰሩ ሲሆን ከቀናት በፊት ሴኔጋል ወደ ግማሽ ፍፃሜው ስታልፍ ኢኳቶሪያል ጊኒን 3 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ በቴክኒክ ክፍል ውስጥ እንደተሳተፉ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ ለዋንጫ ለማለፍ ሴኔጋል ከቡርኪናፋሶ የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢትዮዽያዊው የመሀል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከረዳቶቻቸዉ ሱዳናዊዩ ኢብራሂም አብደላ እና ኬንያዊዩ ጊልበርት ቸሪዮት እንዲሁም ሊቢያዊዩ ፒተር ካማኩ ጋር በመሆን ጨዋታዉን የሚመሩ ይሆናል።

ተጠባቂዉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታም በቡርኪናፋሶ እና ሴኔጋል መካከል ምሽት 04:00 ሰዓት ላይ የሚደረግ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...